የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላዉያን | ኢትዮጵያ | DW | 13.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላዉያን

የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላዉያን ሴቶች የዛሬ ስምንት ዓመት ወደእስራኤል ከመሄራቸዉ አስቀድሞ የወሊድ መቆጣጠሪያ በግዳጅ ተሰጥቶናል ሲሉ ማመልከታቸዉን ሰሞኑን የእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርገዋል።

default

The Time of Israel የተሰኘዉ ድረገፅ እንዳመለከተዉ ጉዳዩን በአንድ የእስራኤል የቴሌቪዥን ጣቢያ ያብራሩት ኢትዮ-ቤተእስራኤላዉያን ወደእስራኤል ለመሄድ ዴፖ ፕሮቬራ የተባለ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት በመርፌ ተሰጥቷቸዋል። ዘገባዉ ባለፉት አስርት ዓመታት 50 ሺህ ኢትዮጵያዉያን አይሁዶች ወደእስራኤል መግባታቸዉን ጠቅሶ፤ ለወትሮ ብዙ ልጅ መዉለድ የሚወደዉ ይህ ማኅበረሰብ በአማካኝ የወሊድ ቁጥሩ 50 በመቶ ቀንሶ መታየቱን አመልክቷል። ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረትን ማግኘቱን ያመለከተዉ እስራኤል ሃይፋ የሚገኘዉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ግርማዉ አሻግሬ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic