የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጉብኝት በበርሊን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 04.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጉብኝት በበርሊን

ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና የመብት ተሟጋቾች ባንፃሩ እዚያዉ በርሊን ዉስጥ ትናንት ባደረጉት ሠልፍ «ሠብአዊ መብት ይረግጣል» ባሉት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጀርመን ተፅዕኖ እንድታሳርፍ ጠይቀዋል

ጠቅላይ ሚንስትር ሐያለ ማርያም ደሳለኝ የመሩት የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የልዕካን ቡድን በጀርመን የሚያደርገዉን ጉብኝት ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል።ቡድኑ በርሊን ዉስጥ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ጨምሮ ከተለያዩ የጀርመን መንግሥት ባለሥልጣናትና ባለሐብቶች ጋር ተነጋግሯል።ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና የመብት ተሟጋቾች ባንፃሩ እዚያዉ በርሊን ዉስጥ ትናንት ባደረጉት ሠልፍ «ሠብአዊ መብት ይረግጣል» ባሉት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጀርመን ተፅዕኖ እንድታሳርፍ ጠይቀዋል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዉይይትና ሠልፉን ተከታትሎታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic