የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጉብኝት በበርሊን | ኢትዮጵያ | DW | 02.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጉብኝት በበርሊን

በጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም የሚመራዉ ቡድን የጀርመንኗን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ጨምሮ የተለያዩ የጀርመን ባለሥልጣናትንና ባለሐብቶችን ለማነጋገር ቀጠሮ አለዉ።ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፤ የኢትዮጵያ ወዳጆችና የሠብአዊ መብት ተሟጋቾች ባንፃሩ እዚያዉ በርሊን ዉስጥ ተቃዉሞ ሠልፍ ለማድረግ አቅደዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመሩት የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የመልዕክተኞች ቡድን ጀርመንን ለመጎብኘት ነገ በርሊን ይገባል።ሥለ ጉብኝቱ አላማና ሒደት እንዲያስረዱን የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ የኮሚኒኬሽን መስሪያቤት እና በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሥልጣናትን ከትናንት ጀምሮ በሥልክ ለማነጋገር ሞክረን ነበር።ነገር ግን በሥልክ ያገኘናቸዉ ፍቃደኞች አይደሉም።ሌሎቹ ደግሞ አልተገኙም። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል እንደሚለዉ ግን በጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም የሚመራዉ ቡድን የጀርመንኗን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ጨምሮ የተለያዩ የጀርመን ባለሥልጣናትንና ባለሐብቶችን ለማነጋገር ቀጠሮ አለዉ።ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፤ የኢትዮጵያ ወዳጆችና የሠብአዊ መብት ተሟጋቾች ባንፃሩ እዚያዉ በርሊን ዉስጥ ተቃዉሞ ሠልፍ ለማድረግ አቅደዋል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic