የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጉብኝት በሳዑዲ አረቢያ | ኢትዮጵያ | DW | 30.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጉብኝት በሳዑዲ አረቢያ

አንዳድ ዘገቦች እንደጠቆሙት የኢትዮጵያ መንግሥት የኮንትራት ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመላክ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

default

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ የመሩት የመልዕክተኞች ጓድ ሳዑዲ አረቢያን እየጎበኘ ነዉ።ጉብኝቱ የሳዑዲ አረቢያን ባለሐብቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብና ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመላክ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።አንዳድ ዘገቦች እንደጠቆሙት የኢትዮጵያ መንግሥት የኮንትራት ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመላክ አዲስ ሕግ አርቅቋል።ይሁንና በጂዳ የዶቸ ቬለ ተባባሪ ዘገቢ ነብዩ ሲራክ እንደሚለዉ ረቂቁ በተለይ የኢትዮጵያዉያንን የሰብአዊ መብት ይዞታ ካላካተተ እስካሁን በኢትዮጵያዉያን የሚደርሱ ችግሮችን ከማባባስ ሌላ የሚተክረዉ የለም።

ቃለመጠይቁን ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምፅ ማጫወቻ ይጫኑ

ነቢዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic