የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤት በሃራሬ እና ዚምባቤዊትዋ ደራሲ | ባህል | DW | 11.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤት በሃራሬ እና ዚምባቤዊትዋ ደራሲ

በዚምባቤ መዲና የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት መጠርያዉ የንግሥት ማክዳ ኢትዮጵያ ሬስቶራንት ይባላል። የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብ በሮበርት ሙጋቤ ሃገር ማስተዋወቅ ከጀመር ወደ 3 ዓመት ተኩል ሆነዉ። በሌላ በኩል ዚምባቤ በትምህርት ጥራት ከአፍሪቃ አንደኛ መሆንዋ ተንግሮላታል። ሕዝቡም ሰላማዊ እንግዳ ተቀባይ ነዉ ተብሎአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 15:37

ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም መጥተዉ አያዉቁም

«የዚምባቤ ሕዝብ በጣም ሰላማዊ ነዉ። ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣናቸዉ ሲወገዱም ሕዝቡ ሽግግሩን እጅግ በሰላማዊ መንገድ ነዉ ያከናወነዉ፤ ሰላማዊነታቸዉ በጣም ያስደንቃል። ዉዝግብ ጭቅጭቅ ወይም ሰዉ አልሞተም»  ስትል የገለፀችልን በዚምባቤ መዲና ሃራሪ የንግሥት ማክዳ ኢትዮጵያ ሬስቶራን ባለቤት ኢትዮጵያዊትዋ ናርዶስ ሌናርድት ናት። ናርዶስ ሊናርድት በሙጋቤ አገር ዚምባቤ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም መኖርያ ሃራሪ ላይ የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብና ቡናን ማስተዋስተዋወቅ ከጀመረች ወደ ሦስት ዓመት ተኩል ሊሆናት እንደሆን ተናግራለች።

ዚምባቤያን የኢትዮጵያ ነገር እንደማይሆንላቸዉ የምትናገረዉ የንግሥት ማክዳ ኢትዮጵያ ሬስቶራን ባለቤት፤ ምግብ ቤታቸዉ ዚምባቤን እንጎብኝ ብለዉ በሚመጡ ቱሪስቶች የታወቀ የተወደደ መሆኑን ሳትገልጽ አላላፈችም። ይህ መሰናዶ በሃራሪ የሚገኘዉን የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቤት ይዞ በጀርመን በርሊን ላይ የተካሄደዉን የአፍሪቃ የመጽሐፍ ፊስቲቫል እንዲመሩ የተመሩ ታዋቂዋ የዚምባቢዌ ደራሲ ሲሲ ዳንጋሬምባን ማንነት ያስተዋዉቃል።  

ባለፈዉ ሳምንት መጠናቀቅያ ላይ ጀርመን መዲና በርሊን ላይ ለአራት ቀናት የተካሄደዉ የአፍሪቃ መጽሐፍ ፊስቲቫል በአፍሪቃ እና በሌሎች የዓለም ሃገራት የሚገኙ አፍሪቃካዉያን ፀሐፍትን ከያንያን አሰባስቦአል። በፊስቲቫሉ የመጽሐፍ ንባብ ጊዜ፤ የልምድ ልዉዉጥና የመወያያ መድረኮች ሁሉ ያካተ ነበር። ይህ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደዉ የአፍሪቃ የመጽሐፍ ፊስቲቫል፤ አፍሪቃዉያን ከያንያን በመድረክ ሙዚቃ እና ትያትር ያቀረቡበትም ነበር። በርሊን ላይ የተዘጋጀዉን የሥነ-ፅሑፍ ፊስቲቫል የመሩት በዚምባቤ ታወቂ የሆኑት ደራሲና የፊልም ሥራ አዋቂ ሲሲ ዳጋሬምባ ነበሩ። በጀርመን መዲና በበርሊን  ለአራት ቀን በተዘረጋዉ  የሥነ-ጽሑፍ መድረክ ዚምባቤዊትዋ ደራሲ እና የፊልም ሥራ አዋቂ መመረጣቸዉን ከተሰማ በኳላ በርግጥ በዚምባቤስ ኢትዮጵያዉያን ይኖሩ ይሆን ብለን ጠየቅን ።  ወደ ፊስቲቫሉ እና ወደ ዚምባቤዊትዋ ደራሲ ሲሲ ዳንጋሬምባ ማንነት ከመጠየቃችን በፊት፤ በሃራሪ የንግሥት ማክዳ ኢትዮጵያን ሬስቶራን ባለቤት ኢትዮጵያዊትዋን  ናርዶስ ሌናርድትን አገኘናቸዉ። ዶይቼ ቬለን ያዳምጣሉ ? የጀርመንን ሬድዮ ያዉቁታል አልናቸዉ። አዎ ግን ብዙ አናዳምጥም እዚህ የምንኖር ኢትዮጵያዉያን ሁላችንም በሥራ የተጠመድን ነን አሉ።

በዚምባቤዋ መዲና ሃራሪ ላይ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቤት መጠርያ ንግሥት ማክዳ ያዉ ንግሥት ሳባም ንግስት አዜብም እንደሆን የምትናገረዉ ወ/ሮ ናርዶስ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ በዚምባቤ ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ እንደታወቀ ነዉ የገለፁት።

የዚምባቤ ከተማ አረንጓዴ ሰላማዊ ፀጥተኛ ከተማ እንደሆነች የነገሩን የንግሥት ማክዳ ኢትዮጵያን ሬስቶራን ባለቤት ናርዶስ ሌናርድት በዚምባቤ ሲኖሩ ወደ 14 ዓመት ሆንዋቸዋል። የዚምባቤ የትምህርት ቤቶች የትምህርት አሰጣጥና እና ስልጠና ከአፍሪቃ አንደኛ መሆኑ ሁሉ በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል።

ዚምባቤ ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ ባደረገችዉ የነጻነት ትግል ኢትዮጵያ ድጋፍ በመስጥት ቀዳሚዉን ስፋራ በመያዝዋ በዚምባቤ ማኅበረሰብ ልብ ታትሞ የሚገኝ ታሪክ መሆኑን የዚምባቤ ተወላጆች ይናገራሉ። ባለፈዉ ሳምንት መጠናቀቅያ ላይ ጀርመን መዲና በርሊን ላይ ለአራት ቀናት የተካሄደዉ የአፍሪቃ መጽሐፍ ፊስቲቫል በአፍሪቃ እና በሌሎች የዓለም ሃገራት የሚገኙ አፍሪቃዉያን ፀሐፍትን ከያንያን አሰባስቦአል። በርሊን ላይ የተዘጋጀዉን የሥነ-ፅሑፍ ፊስቲቫል የመሩት በዚምባቤ ታወቂ የሆኑት ደራሲና የፊልም ሥራ አዋቂ ሲሲ ዳጋሬምባ ነበሩ። ባለፈዉ ሳምንት ሃሙስ በተጀመረዉ እና እሁድ እለት የተጠናቀቀዉ መድረክ አዘጋጆች የዚምባቤዋን ደራሲ ጋብዘዉ ባደረጉት ንግግር

« በዚምባቤ እጅግ የታወቂ የሆኑትን ፀሐፊና የፊልም ሥራ አዋቂ ሲሲ ዳጋሬምባ በበርሊን የ 2019 የአፍሪቃ የሥነ ጽሑፍ ፊስቲቫል እንዲመሩ መርጠናቸዋል። የወንዶች የበላይነት በሚታይባት በዚምባቤ ሲሲ ዳንጋሬምባ በሴቶች ጉዳይ ሳያቋርጡ ድምጻቸዉን ከፍ አድርገዉ የሚናገሩና ለመብት የሚሟገቱ በመሆናቸዉ ይታወቃሉ። ሲሲ ወጣት ሳሉ በ 25 ዓመታቸዉ በጎርጎረሳዉያኑ 1988 ዓም     « Nervous Condition » የሚያስጨንቅ ወይም የሚረብሽ ሁኔታ የተሰኘዉን መጽሐፍ ለአንባቢ  አቅርበዋል። »

ዚምባቤዊትዋ ደራሲ ሲሲ ዳጋሬምባ የፆታ እኩልነት ተግባራዊነት ሲጠቀስ ቀዳሚ ትብብር በሚለዉ መርህ በትልቅ ምሳሌነት ይጠቀሳሉ። ደራሲዋ በ 30 ዓመት ሞያዊ ልምዳቸዉ በዓለም አቀፍ ደረጃ 4 ጊዜ ተሸልመዋል። በፊልም ሥራ ሞያቸዉም ይታወቃል። 

«ሲሲ ዳንጋሬምባ ድምፃቸዉን የሚያሰሙት ድምፅ ለሌላቸዉ ብቻ ሳይሆን፤ በሃገራቸዉ በስልጣን ላይ ከሚገኙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ለመደራደር እና ለመከራከር አያፈገፍጉም። ያላቸዉን እዉቀትም ለትዉልድ በማሳለፍ እንዲማሩበት አዲስ ነገር እንዲፈጥሩበት እገዛ ያደርጋሉ። ሲሲ በሃራሬ «ዓለም አቀፍ የሴቶች  ምስል ፊስቲቫል» የሚል በየዓመቱ የሚካሄድ መድረክንም  መስርተዋል፤ በዚምባቤ የሴቶች የፊልም ስራ ድርጅት አባል በመሆን በፊልም ሥራ ላይ የተሰማሩ ሴቶችንም ይረዳሉ።   

« Nervous Condition » የሚያስጨንቅ ወይም የሚረብሽ ሁኔታ የሚል ርዕስን የሰጡት መጽሐፋቸዉ ፤ በዚምባቤ ከአንዲት ጥቁር ሴት የተፃፈ የመጀመርያ መጽሐፍ ነዉ። የፀሐፊዋ ይህ ድርሰት በጎርጎረሳዉያኑ 1989 ዓም የኮመን ዌልዝ የፀኃፊያን ሽልማትን አግኝቶአል። BBC የብዙኃን መገናኛ ጣብያ በኩሉ ይሄዉ መጽሐፍ ዓለማችንን የቀየሩ 100 የዓለም ድርሰቶች መካከልም አካቶታል። ዚምባቤዊትዋ ታዋቂ ደራሲ በቅርቡ «This Mournable Body» አሳዛኙ አካል በሚል አዲስ መጽሐፍን ለአንባብያን አቅርበዋል።  

« ሴቶች በብሔራዊ፤ በአህጉራዊ ፤ በዓለምአቀፋዊ እና በባህላዊ ትስስሮች እና ግንኙነቶች ሥራ ላይ መሳተፉ መጀመራቸዉን ማየት እጅግ ያስደስታል። ይህ መድረክም ለዚህ ተስማሚ ሆኖ መጀመሩን ማየት ያስደስታል። » ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ። 

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic