የኢትዮጵያ ቡድን በአፍሪቃ እግር ኳስ ግጥሚያ | ኢትዮጵያ | DW | 29.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ቡድን በአፍሪቃ እግር ኳስ ግጥሚያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሐያ-ዘጠነኛዉ የአፍሪቃ እግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያ መቀጠል-አለመቀጠሉ ከግማሽ ሠዓት በሕዋላ ከናይጄሪያ ባላጋራዉ ጋር በሚያደርገዉ ግጥሚያ ዉጤት ይወሰናል።

ከሰላሳ-ዓመት በሕዋላ ከትልቁ ዉድድር የገባዉ ኢትዮጵያ ቡድን ለሚቀጥለዉ ዙር ለማለፍ ወደ ሜዳ የሚገባዉ ከጠባብ ዕድል ጋር ነዉ።ማሸነፍ ብቻ።ኢትዮጵያዉያን ተጫዋቾች ከዚሕ ቀደም የዛምቢያ ባላጋራቸዉን ሲገጥሙ ያሳዩትን አይነት ያጨዋወት ጥበብ፥ ቅልጥፍና፥ ጥንካሬ እና ከሁሉም በላይ በራስ የመተማመን ብርታን ከደገሙት ኢትዮጵያዉያን ስፖርት አፍቃሪዎችን «ማታ ነዉ ድሌን ሊዘፍኑ» ቢዘጋጁ ይገባቸዋል።ተጨዋቾቹ ባለፈዉ አርብ ከቡርኪና ፋሶ ቡድን ጋር ሲጋጠሙ የነበሩት አይነት ከሆኑ ግን-ተመልካቹ ለትካዜ፥ ተጨዋቾቹ ጓዛቸዉን ለመጠቅለል መዘጋጀት ግድ ነዉ-የሚሆንባቸዉ።ግጥሚያዉን እዚያዉ ደቡብ አፍሪቃ ሆና የምትከታተለዉ ሐይማኖት ጥሩነት  የኢትዮጵያ ቡድን ደጋፊዎችን አነጋግራለች።

ሐይማኖት ጥሩነህ

ነጋሽ መሀመድ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic