የአትሌት አበበ ቢቂላናደራርቱ ቱሉ መታሰቢያ ዝግጅት በፈረንሳይ
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 4 2016ማስታወቂያ
የፓሪስ ኦሎምፒክ በሚካሄድበት በዚሁ ወቅት ቀዳሚ አትሌቶች አበበ ቢቂላና ደራርቱ ቱሉን የሚዘከሩበት ስነስርአት በፈረንሳይ ከፓሪስ ከተማ በስተሰሜን በምትገኘው በኢልሳንደኒ ተካሂዷል።
በዚሁ የኢትዮጵያ ቀን የሚዘከርበት አውደርእይ የአትሌት ደራርቱ ቱሉን የኦሎምፒክ ገድል የዘከረ ዘጋቢ ፊልምና የፎቶ አውደ ርእይ ቀርቧል። በዚሁ የኢትዮጵያ ቀን ልዩ ዝግጅት ላይ የሮምን የቶክዮ ኦሎምፒክ ባለድሉ አትሌት አበበ ቢቂላ ሥራዎችም ቀርበዋል።
በዝግጅቱ የታደሙ ኢትዮጵያውያን ለDW በሰጡት አስተያየት በዚሁ መድረክ የኢትዮጵያውያኑ የኦሎምፒክ ገድል መቅረቡ ልዩ ስሜት እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር