የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት የፍርድ ቤት ውሎ | ኢትዮጵያ | DW | 06.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት የፍርድ ቤት ውሎ

አቶ አብዲ መሐመድ በዋና ወንጀል ፈጻሚነት እና አመራር በመስጠት ለ59 ሰዎች ኅልፈት፤ 266 ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸው፤ ከ412 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ላላቸው ንብረቶች ውድመት ተጠያቂ አድርጓቸዋል አቃቤ ሕግ በክሱ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:01

የቀድሞዉ የኢትዮ-ሶማሌ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር የተመሰረተባቸዉን ክስ ዉቅድቅ አደረጉት


የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚደንት አብዲ መሐመድ የቀረበባቸው ክስ «የተቀነባበረ» መኾኑን ዛሬ ለፍርድ ቤት ተናገሩ።  አቶ አብዲ ይኽን የተናገሩት፦ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ በቀረቡበት ወቅት ነው። አቶ አብዲ መሐመድ በዋና ወንጀል ፈጻሚነት እና አመራር በመስጠት ለ59 ሰዎች ኅልፈት፤ 266 ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸው፤ ከ412 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ላላቸው ንብረቶች ውድመት ተጠያቂ አድርጓቸዋል አቃቤ ሕግ በክሱ። አቶ አብዲ ክሱ ገብቷቸው እንደኾን በዳኞች ተጠይቀው፦ «ክሱ በውሸት የተቀነባበረ መኾኑ ገብቶኛል» ማለታቸውን የፍርድ ቤት ውሎውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ዘግቧል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic