የኢትዮጵያ ሥራ አጥ ቁጥር እንዴት ይሰላል? | ኤኮኖሚ | DW | 03.07.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያ ሥራ አጥ ቁጥር እንዴት ይሰላል?

የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ 2012 ዓ.ም. የበጀት አመት መጨረሻ 3 ሚሊዮን የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱን አስታውቋል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ሰኞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባሰሙት ንግግር የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሥራ አጥ ቁጥር ከ11 ሚሊዮን በላይ መድረሱን አስረድተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 15:35

የኢትዮጵያ ሥራ አጥ ቁጥር እንዴት ይሰላል?

ጠቅላይ ምኒስትሩ እንዳሉት በየአመቱ ከ2 ሚሊዮን ያላነሰ የሰው ሀይል ወደ ሥራ ፈላጊው ገበያ ይቀላቀላል ተብሎ ይገመታል። ጠቅላይ ምኒስትሩ «ኤኮኖሚው እስካሁን በአመት የሚፈጥረው የሥራ ዕድል ከአንድ ሚሊዮን እምብዛም አይዘልም።  ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል የተቋቋመው ኮሚሽን ወደ ተግባር ገብቷል። እስከ መጪው የበጀት አመት መጨረሻ ድረስ ለሶስት ሚሊዮን ዜጎች በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ ሲሆን በ2011 በጀት አመት ለ1.4 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል። በአብዛኛው የተፈጠሩት የሥራ ዕድሎች የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማትን በመጠቀም የተፈጠሩ ናቸው። የተፈጠረው የስራ ዕድል ቀደም ባሉት አመታት ከነበረው የተመሳሳይ ወቅት አፈፃጸም ያላነሰ ቢሆንም ካለን ከፍተኛ የሥራ ፈላጊ ቁጥር አንፃር በቂ ነው የሚባል አይደለም» ሲሉ ተናግረዋል።

ለመሆኑ የኢትዮጵያ የሥራ እና የሥራ አጥነት መረጃ እንዴት ይሰበሰባል? በንድፈ-ሐሳብ ሥራ ኖሯቸው ከአቅም እና ክሕሎታቸው በታች የሚሰሩ ዜጎች ጉዳይስ? በኢ-መደበኛው ኤኮኖሚ ውስጥ ያለው መረጃ እንዴት ይሰበሰባል?

ሙሉ መሰናዶውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ፦

እሸቴ በቀለ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic