የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብትና የዓለም ባንክ | ኤኮኖሚ | DW | 25.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብትና የዓለም ባንክ

የኤኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ በጋሻዉ ግን ሁለቱ ተቋማት የአሜሪካና የአዉሮጳን ጥቅም ከማስከበር አልፈዉ ለአፍሪቃ የሚረዳ ነገር መክረዉ፤አድርገዉም አያዉቁም።ኢትዮጵያም የዕዳዋን መጠን ለመቆጣጠር የራስዋን ጠቃሚ መርሕ መከተል ነዉ የሚገባት።

default

ኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብቷን ይበልጥ ለማሳደግ ሁለት መሠረታዊ እርምጃዎችን እንድተወስድ የዓለም ባንክ እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት እየጎተጎቱ ነዉ።በሁለቱ ተቋማት ሁለት ጥቆማ-መሠረት ኢትዮጵያ ያለባትን ዕዳ ማቃለል እና፤ የብር የምንዛሪ ዋጋን መቀነስ አለባት።የኤኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ በጋሻዉ ግን ሁለቱ ተቋማት የአሜሪካና የአዉሮጳን ጥቅም ከማስከበር አልፈዉ ለአፍሪቃ የሚረዳ ነገር መክረዉ፤አድርገዉም አያዉቁም።ኢትዮጵያም የዕዳዋን መጠን ለመቆጣጠር የራስዋን ጠቃሚ መርሕ መከተል ነዉ የሚገባት።የብር ዋጋን መቀነስ ግን ፕሮፌሰሩ እንደሚመክሩት እስካሁንም ካለዉ የባሰ የዋጋ ንረትና፤የኑሮ ዉድነትን የሚያስከትል ነዉ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic