የኢትዮጵያ ምርጫ ይፋ ዉጤት፥ ዉዝግቡና ክሱ | ኢትዮጵያ | DW | 21.06.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ምርጫ ይፋ ዉጤት፥ ዉዝግቡና ክሱ

አስር ሰአት ላይ ግን ዉጤቱ አልተነገረም።ምክንያቱ፥- የአለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያ የቴሌቪዥን ሥርጭት እስከሚጠናቀቅ የሚል ነዉ።

default

ምርጫ

21 06 10

ዛሬም እንደገና ባለፈዉ ግንቦት አስራ-አምስት ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ አስታከን ዉጤቱን፥ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አቋምና የፍርድ ቤት ሙግትን አንስተን የሁለት ተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናትንና የአዲስ አበባ ወኪላችንንን አነጋግረናል።ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈዉ ግንቦት አስራ-አምስት የተደረገዉን ምርጫ የመጨረሻ ዉጤት ዛሬ-ረፈዱ ላይ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ነበር።አላደረገም።ተዛዋረ።ምክንያት፣- የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንደነገረን-ምክንያት አልተሰጠም።
የምርጫዉ የመጨረሻ ዉጤት ምንም ሆነ-ምን ስምንት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚያስተናብረዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ባለሥልጣናት እንዳሉት ፓርቲያቸዉ የሚጠብቀዉ ነገር የለም።የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢና የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እንዳሉት ፓርቲያቸዉ በፍርድ ቤቱ ሙግት ይቀጥላል።

እንደ መድረክ ሁሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን የከሰሰዉ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ከሚለዉ ዉጤት የሚጠብቀዉ የለም።የድርጅቱ የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ያዕቆብ ልኬ ፓርቲያቸዉ ይሕን አቋም ለመያዙ ብዙ ምክንያት

Dr. Negasso Gidada

ዶ/ር ነጋሶ

ይዘረዝራሉ።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻዉን ዉጤት ለማስታወቅ ለዛሬ ጧት አምስት ሰአት ይዞት ሰጥቶት የነበረዉን ቀጠሮ የቀየረዉ ወደ አስር-ሰአት ነበር።አስር ሰአት ላይ ግን ዉጤቱ አልተነገረም።ምክንያቱ፥- የአለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያ የቴሌቪዥን ሥርጭት እስከሚጠናቀቅ የሚል ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic