የኢትዮጵያ ምርጫ ውጤትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 23.06.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ምርጫ ውጤትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

ግንቦት 16, 2007 ዓ,ም የተካሄደዉ 5ኛው አጠቃላይ ብሔራዊ ምርጫ ገዥዉ ፓርቲ «ኢ ሕ አ ዴ ግ»ና አጋር ድርጅቶች ማሸነፋቸዉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታዉቆአል። የተለያዩ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውጤቱ ተቀባይነት የለዉም ሲሉ ለዶይቼ ቬለ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:58
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:58 ደቂቃ

የኢትዮጵያ ምርጫ ውጤትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ግንቦት 16 2007 ዓ,ም የተካሄደዉን ምርጫ የመጨረሻ ዉጤት ትናንት ከቀትር በኋላ ይፋ ካደረገ በኋላ የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶች የምርጫ ሂደቱ የተጭበረበረ ስለነበር ዉጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል የታወቀ እንደነበር ተናግረዋል። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት፤ ምርጫ ነበረና ምርጫ ተደረገ የሚያሰኝ ነገር አልነበረም ነዉ ያሉት። እንድያም ሆኖ አሁን መድብለ ፓርቲ አበቃለት ማለት አይቻልም ብለዋል።

ምክንያቱም መድብለ ፓርቲ የሚያበቃለትም ሆነ የሚመሰረተዉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ። በይፋዊ ዉጤቱ የገዥዉ ፓርቲ ወዳጆች ብቻ ሳይሆኑ ራሱ ገዥዉ ፓርቲም ተደናግጦበታል፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፊደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት አንድነት በአጭሩ ምክትል ሊቀመንበርና የፓርቲዉ የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ዶክተር መረራ ጉዲና በበኩላቸዉ የምርጫዉ ዉጤት በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ሊታሰብ የማይችል ሲሉ ነዉ የገለፁት።

በአቶ ትዕግስቱ አወሉ የሚመራዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ደግሞ «ኢ ሕ አ ዴ ግ» መቶ በመቶ ማሸነፉ የተነገረን የምርጫ ዉጤት በሂደቱ ብዜ ችግሮች ነበሩት ፤ በቶ በመቶ የሚለዉ ነገር በግሌ የማላምንበት ነዉ ፤ ፓርቲዉ ግን በቅርቡ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic