የኢትዮጵያ ምርጫ ዉጤት | ኢትዮጵያ | DW | 10.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ምርጫ ዉጤት

አብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫዉ ባለመሳተፋቸዉ ገዢዉ ፓርቲ እንደሚያሸንፍ ከምርጫዉ በፊትም የታወቀ ነበር።የብሔራዊ አስመራጭ ቦርድ ባለሥልጣናት ዛሬ እንዳሉት ግን የተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫዉ አለመሳተፍ የምርጫዉን ሒደት ሠላማዊና ፍትሐዊነት አላጓደለዉም


ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለፈዉ ሚዚያ ሥድስትና አሥራ-ሰወስት በተደረገዉ የአካባቢና የከተማ መስተዳድሮች ምርጫ ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግና ተባባሪዎቹ ፓርቲዎች እንደተጠበቀዉ ማሸነፋቸዉ ተረጋገጠ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ እንዳስታወቀዉ ኢሕአዲግና ተባባሪዎቹ ፓርቲዎች ካቀረቧቸዉ ዕጩዎች ሌላ በምርጫዉ ያሸነፉት አምስት ሰዎች ብቻ ናቸዉ።አብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫዉ ባለመሳተፋቸዉ ገዢዉ ፓርቲ እንደሚያሸንፍ ከምርጫዉ በፊትም የታወቀ ነበር።የብሔራዊ አስመራጭ ቦርድ ባለሥልጣናት ዛሬ እንዳሉት ግን የተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫዉ አለመሳተፍ የምርጫዉን ሒደት ሠላማዊና ፍትሐዊነት አላጓደለዉም።ድምፁን ለመስጠት ከተመዘገበዉ ከ31 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ከዘጠና ሁለት ከመቶ የሚበልጠዉ ድምፁን መስጠቱንም የቦርዱ ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic