የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና ተቃዋሚዎች | ኢትዮጵያ | DW | 16.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና ተቃዋሚዎች

ማስረጃ በሌለው ጉዳይ ላይ ምንም ማድረግ እንዳልቻለ ያስታወቀው የምርጫ ቦርድ የመወዳደሪያ ምልክት መውሰጃ የጊዜ ገደብ ታህሳስ 20 በመጠናቀቁ ፓርቲዎቹ በምርጫው እንደማይሳተፉ የተወቀ ጉዳይ ነው ብሏል ።

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Erklärung der Wahlprozedur in Oromia, Äthiopien 23.Mai 2010 Thema: bei Äthiopiens Parlamentswahl 2010 erklärt dieser Wahlhelfer Wählern in Debre Zeit, Oromia, die Wahlprozedur Schlagwörter:Wahl Äthiopien 2010, Stimmabgabe, Polls, Voting Ethiopia 2010

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ፣ 33 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከቀጣዩ አካባቢያዊና የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫ ስለማግለላቸው የደረሰው ነገር እንደሌለ አስታወቀ ። ፓርቲዎቹ የምርጫ ቦርድ ችግራችንን ሊፈታልን አልቻለም ሲሉ ያቀረቧቸው ጥያቄዎችም አዲስ እንዳልሆኑና በማስረጃም እንዳልተደገፉ ገልጿል ። ማስረጃ በሌለው ጉዳይ ላይ ምንም ማድረግ እንዳልቻለ ያስታወቀው የምርጫ ቦርድ የመወዳደሪያ ምልክት መውሰጃ የጊዜ ገደብ በማለፉ በመጠናቀቁ ፓርቲዎቹ በምርጫው እንደማይሳተፉ የተወቀ ጉዳይ ነው ብሏል ። የፓርቲዎቹ ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ከመንግሥትና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ለመወያየት ፓርቲዎቹ በተደጋጋሚ ያቀረቡት ጥያቄ ዉድቅ ሥለሆነባቸዉ እራሳቸዉን ከምርጫዉ ለማግለል መገደደቸውን ትናንት አስታውቀዋል ። ዝርዝሩን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘአብሔር ያቀርብልናል

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic