የኢትዮጵያ ምርጫ ሒደትና አስተምሕሮቱ | ኢትዮጵያ | DW | 24.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ምርጫ ሒደትና አስተምሕሮቱ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች-በመድረክ ከፍተኛ መሪ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ቋንቋ «ምርጫ አይመስልም ነበር-በአፍሪቃ መመዘኛ እንኳን!» በማለት አጣጥለዉታል።ገዢዉ ፓርቲ ባንፃሩ በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አገላለፅ «ሰዎች ከድምፅ መስጪያ ክፍል አንዴ ከገቡ-የሚያስደስታቸዉን ይመርጣሉ

default

ዶ/ር ነጋሶ ከተቃዋሚ መሪዎች አንዱ

24 05 10

ሒደቱ-አሁንም እያወዛገበ ነዉ።ዉጤቱ ገና አልታወቀም።ወይም በተቃራኒዉ አንዳዶች እንደሚሉት ከመነገሩ በፊት ታዉቋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በርግጥ ድምፁን ሰጥቷል።ሒደቱ የማወቃቀስ-ማወዛገቡን ያክል-አስተምሕሮቱም ያነጋግራል።የዛሬ ትኩረታችን ነዉ።ከሕግና ከፖለቲካ ሳይንስ ምሑር ከዶክተር ለማ ይፍራ ሸዋ ጋር ላፍታ እንነጋገር።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች-በመድረክ ከፍተኛ መሪ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ቋንቋ «ምርጫ አይመስልም ነበር-በአፍሪቃ መመዘኛ እንኳን!» በማለት አጣጥለዉታል።ገዢዉ ፓርቲ ባንፃሩ በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አገላለፅ «ሰዎች ከድምፅ መስጪያ ክፍል አንዴ ከገቡ-የሚያስደስታቸዉን ይመርጣሉ።» ነፃ-ነዉ-እንደማለት።የአዉሮጳ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድን መሪ ቲስ ቤርማን-«ጣቢያዎች በቅጡ የተደራጁበት፥ ብዙ ሕዝብ ድምፅ የሰጠበት ሠላምና ፀጥታ የሠፈነበት ነዉ»።-ምርጫዉ። ለዶክተር ለማ ይፍራ

Meles Zenawi Ministerpräsident Äthiopien

ጠ/ሚ መለስ

ሸዋ ደግሞ ከዚሕም በላይ ነዉ።

====================

የ1997ቱ ምርጫ ከዘንድሮዉ ጋር የመነፃፀሩ ምክንያት «ቀን እባብ ያየ ማታ በልጥ በረየ ብሎ አባባል አይነት ከሆነ በርግጥ እንደገና ያጠያይቃል።ለምን? ብቻ ዶክተር ለማ ይቀጥላሉ።

====================

ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ገና የምረጡኝ ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ወቀሳና ሥሞታ የተቀበለበት ጊዜ የለም።በትናንቱ የድምፅ አሰጣጥ ሒደትም የገዢዉ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች አደረሱት የተባለዉን በደል እንደማይቀበሉት ባለሥልጣናቱ በተደጋጋሚ አስታዉቀዋል።

የትናንቱ ምርጫ ዉጤት ገና እየተጠበቀ ነዉ።ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ግን የሚመሩት ፓርቲ እንደሚያሸንፍ ለመናገር እስከ ዉጤቱ አይደለም እስከ ዛሬ መጠበቅም አላስፈለጋቸዉም።ትናንት ተናገሩት።ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢሕዴግ ያሸንፋል ለማለት ምክንያት ያደረጉት ግን መንግሥታቸዉ አሳየ ያሉትን የምጣኔ ሐብት እድገት ነዉ።

Erklärung der Wahlprozedur in Oromia Äthiopien 23.Mai 2010

መረጡ

«ለሰባት አመታት ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበ መንግሥት በምርጫ ሲሸነፍ እስኪ አስቡት?» ጠየቁ አሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠያቂ ጋዜጠኞችን-ሮይተርስ እንደዘገበዉ።«በዚች ምድር የትም ቦታ መቼም ሆኖ አያዉቅም» አከሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ።ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባንፃሩ ገና ሲጀመር ኢሕአዴግ ካላጭበረበረ በስተቀር የምናሸንፈዉ እኛ ነን እንዳሉ ነዉ።

ዶክተር ለማ ግን ዉጤቱ ምንም ሆነ ምን መሠረቱ ሌላ ነዉ ባይ ናቸዉ።ሁሉም ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ያለነሱትን፥ ወይም ሆን ብለዉ ያሳነሱትን ትንሽ መሳይ ግን ትልቅ ነገር ያነሳሉ።በ2000 (እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር 2008 ) የተደረገዉን የቀበሌና የወረዳ ምክር ቤቶች ምርጫ።

====================

ዶክተር ለማን አመሰግናለሁ።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

ከዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic