የኢትዮጵያ ምርጫና ዩናይትድ ስቴትስ | ዓለም | DW | 26.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኢትዮጵያ ምርጫና ዩናይትድ ስቴትስ

በገዢዉ ፓርቲ ተፅዕኖ ሲደረግበት ነበር።የፀጥታ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ማይክ ሐመር እንደሚሉት ገለልተኛ ወገኖች የምርጫዉን ሒደት እንዳይከታተሉ ታግደዋል፥ ነፃ መገናኛ ዘዴዎችም ጫና ተደርጎባቸዋል

default

ምርጫዉ

ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉ ምርጫ ዉጤትና ሒደት እንዳሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች። የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤትና የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባለሥልጣናት በየፊናቸዉ እንዳሉት የምርጫዉ ሒደት በገዢዉ ፓርቲ ተፅዕኖ ሲደረግበት ነበር።የፀጥታ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ማይክ ሐመር እንደሚሉት ገለልተኛ ወገኖች የምርጫዉን ሒደት እንዳይከታተሉ ታግደዋል፥ ነፃ መገናኛ ዘዴዎችም ጫና ተደርጎባቸዋል።የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጂኒ ኮርሰን በበኩላቸዉ ምርጫዉ አሁን ያለዉን አይነት ዉጤት እንዲኖረዉ ኢትዮጵያ መንግሥት ከአስራ-ስምንት ወራት በፊት ጀምሮ ተፅኖ ሲያደርግ ነበር ይላሉ።ሥለ መግለጫዎቹ ነጋሽ መሐመድ የዋሽንግተኑን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሮት ነበር።

-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------

የዩናይትድ ስቴትስ

United States State Department Washington Außenansicht

የአሜሪካ ዉጉሚ ሕንፃ

ባለሥልጣናት ሥለ ኢትዮጵያ ምርጫ የተነጋሩት ከዲፕሎማሲያዊ ቃላት ባለፍ ሌላ መልዕክት እንደሌለዉ አንድ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ጉዳይ አዋቂ ተናግረዋል።የምሥራቅ አፍሪቃ የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲን እንደሚሉት ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ መንግሥት ምርጫዉን አጭበርብሮ ብላ ብታምን እንኳን በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ እርምጃ ለመዉሰድ የተዘጋጀች አትመስልም።አቶ ዩሱፍ እንደሚያምኑት ከዋሽንግተን የሚሰማዉ የ«አሳስቦናል መግለጫ»ም የኢትዮጵያ መንግሥትንም ብዙ አያሳስብም።አቶ ዩሱፉን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic