የኢትዮጵያ ምርጫና የምሁሩ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 22.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ምርጫና የምሁሩ አስተያየት

በቅርቡ ባስነበቡት መጣጥፋቸው፤ አንዳንድ ኃያላን መንግሥታት እዚህም ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ፣የአንዳንድ መንግሥታትን የምርጫ ሂደት አክብራ በገለልተኝነት ስትመለከት በሌሎች ጣልቃ የመግባት ዝንባሌ እንዳሳየች ገልጸዋል። ፈላጭ -ቆራጭ መንግሥታትን

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:05

የኢትዮጵያው የምርጫ ሂደት ይዞታ በአንድ የኤኮኖሚ ምሁር እይታ

በአያያዛቸው እንዲቀጥሉ መደገፍ ብቻ ሳይሆን፣ ጣልቃ የመግባት ምልክት አሳይታለች ያሉትን ፤ ከለንደን «ስኩል ኦፍ ኤኮኖሚክስ» ፤ የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ተንታኝ ዶ/ር አወል ቓሲም አሎን ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የፊታችን እሁድ የሚካሄደውን የኢትዮጵያውን ምርጫ መነሻ በማድረግ ፤ የዶይቸ ቨለው ሉድገር ሻዶምስኪ በስልክ አነጋሮአቸዋል። ዶ/ር አዎል በመጀመሪያ የኤኮኖሚ ዕድገትንና የዴሞክራሲን ፣ የሰብአዊ መብት ይዞታን በተመለከተ አስተያየታቸው ምን እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ተከታዩን ማብራሪያ ነበረ የሰጡት።

«እንደሚመስለኝ ፤ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ በዐይን የሚታይ የኤኮኖሚ ግሥጋሴ ታይቷል። ይህ የሚካድበት ምክንያት የለም። ይሁንና ከዚያ ውጭ እጅግ ጨቋኝ የሆነ ሥርዓት (መንግሥት) ነው ያለው። የሰላ ሒስም ሆነ ትችት የሚያቀርቡትን ሁሉ ማጥፋት ነው የሚታየው። ይህም የተቃውሞ ፓርቲዎችን ፖለቲከኞችን ፣ ጋዜጠኞችን የድረ-ገጽ ዓምደኞችን፤ የማሕበረሰብ መሪዎችንና የመሳሰሉትን ሁሉ ያጠቃልላል። እንደማስበው እነዚህ ሁሉ እርስ በርስ ማስታረቅ በጭራሽ የማይቻል ነው።በመሠረቱ፣ በኤኮኖሚው መስክ፤ በዚያው ልክ ደግሞ ዴሞክራሲናና ሰብአዊ መብትን በተመለከተ ከ 19977 ወዲህ እያሽቆለቆለ መሄዱ ነው የሚታየው።»

የተቃውሞ ፓርቲዎችን አቋም ፤ ይዞታ እስቲ ባጭሩ እንዳስስ፤ በሕዝብ ዘንድ ጆሮ ያገኘ መጥቆ የወጣ አንድ ፓርቲ አለ -በኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት የሚመራው ሰማያዊ ፓርቲ! ይህ ፓርቲ በተለይ ከወጣቶች በኩል ሰፋ ያለ ድጋፍ ያገኘ ይመስላል፤ ማራኪነት ያገኘው በምን ምክንያት ይመስሎታል? ምናልባት ቆየት ያሉትን የተቃውሞ ፓርቲዎች የመሰልቸት ሁኔታ ተፈጥሮ ይሆን?

«የትና እንዴት የሚለውን ሁኔታ የመመልከት ጉዳይ ነው። ለማሳሌ አዲስ አበባን ከወሰዱ ምናልባት ሰማያዊ ፓርቲ ከሞላ ጎደልበአቀራረቡ ላቅ ያለ ተሰሚነት አግኝቶ ይሆናል። ቀሪውን ያገሪቱን ክፍል 75 ከመቶውን ከተመለከቱ ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ እጅግ ጠንካራ ፓርቲ ነው ለማለት ያስቸግራል። ሰማያዊ ፓርቲ ማራኪ የሆነበት ምክንያት ለእኔ ግልጽ አይደለም። ፓርቲው የቆዩ የኢትዮጵያ ጥንታዊ የመንግሥትነት ሐሳቦች የሚያንጸባርቅ ይመስላል። ይህ ሐሳብና ፍልስፍና ለሌሎች፤ ለአብዛኛዎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ማራኪነት ያለው ስለመሆኑ ለአኔ ግልጽ አይደለም። በእርግጥ የዚህ ፓርቲ አባል የሆነው በከፊል ወጣቱ ትውልድ፣ በመገናኛ ብዙኀን በመገናኛ መረብ ፤ ወጣቱ በሚጠቀምበት የመገናኛ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፤ ሕዝብ ማሰባሰብና ፓርቲው ትኩረት እንዲሰጠው አብቅተው ይሆናል። ይሁንና የፓርቲው ፤ ማራኪነት ከአዲስ አበባ ውጭ ያለው ድጋፍ ፤ እስከምን ድረስ እንደሆነ ለእኔ ግልጽ አይደለም።»

ገዥው ፓርቲ ኢ ሕ አ ዴ ግ ፤ የዘንድሮውን ምርጫም በአሸናፊነት ለመወጣት ተዘጋጅቷል። በ 2002 ዓ ም 99,6 ከመቶ የፓርላማ መናብርትን መያዙ የሚታወስ ነው። በአሁኑ ምርጫ ዋናው ርእሰ ጉዳይ ምንድን ነው? ጠ/ሚንስትር ኃ/ምርያም ደሳለኝ ፣ ሥልጣናቸውን አጥብቀው እንደሚይዙ የሚያተጋግጥ ይሆናል ወይ? ሌላው ሉድገር ለዶ/ር አዎል ያቀረበው ጥያቄ ነበር።

«ሀገሪቱን በማስተዳደር ረገድ ዋናው ተቆጣጣሪ ናቸው ማለት አያቻልም፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቢጠየቅ በሥልጣን የመንግሥትን ሥራ የሚመሩ ሌሎች ስለመኖራቸው የሚናገረው ነው። ጠ/ሚንስትሩ በዋናነት መማራት እንዳልቻሉ መቆጣጠር እንደተሣናቸው ማሳያው፤ የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ከሞቱ በኋላ፤ አመራሩ ከግለሰብ እጅ ወደ ወደ ቡድን ወይም ስብስብ ሽግግር ማድረጉ ነው። የፓርቲ ከፍ,ተኛ አመራር አባላት ስብስብ ወይም የአገዛዝ ስbnብስብ ሲባል፤ ጠ/ሚንስትሩ አሉ፤ ሆኖም ሌሎች ሚንስትሮች፤ በዙሪያቸው ሆነው ፖሊሲ እንዲቀረጽና ውሳኔ እንዲተላለፍ ተጽእኖ የሚያደርጉ እነርሱው ናቸው። በቀጣይነት ከምናየው አገዛዝ አንጻር ፣ስለዴሞክራሲ ፤ ሰብአዊ መብት ፣ በሰፊው ሲታይም ስለሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ የሚያሳስባቸው ወገኖች በአስቸጋሪ ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ልብ ይላሉ። አብዛኞቹ የአገሪቱ ተወላጆች፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ በመናጥ ላይ ስላለች ሀገራቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሐሳባቸውን ለመግለጽ ሳይችሉ ቆይተዋል።»

እስካሁን ከቀጠለውና ከሚቀጥለው አስተዳደር አንጻር ለዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት እሴቶች የሚቆሙ ወገኖች አሉ፤ የአገሪቱ መጻዔ ዕድል ምን ሊሆን ይችላል?

«በአሁኑ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርዓት፣ አንዳንድ ብሔረሰቦች፤ ወደ ጠርዝ ነው የተገፉት። ይህ በፊናው የሚንፈቀፈቅ ምሬት አዝሎ ጊዜውን የሚጠብቅ ነው የሚሆነው። ያ ደግሞ እንደሚመስለኝ ቀውሱን መወጣት የሚቻልበት ያገሪቱ ዕድልም ሆነ ችሎታ እስከዚህማ የሚያወላዳ ላይሆን ይችላል።እንደሚመስለኝ ፣ ይህ ምርጫ ወሳኝነት ያለው ነው። ኢ ሕ አ ዴ ግ ማሸነፉ አይቀሬ ነው። ነገር ግን ይህ ለሀገሪቱ ምን ማለት ይሆናል? ይህ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic