የኢትዮጵያ ሚና በአፍሪቃ | ኢትዮጵያ | DW | 24.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ሚና በአፍሪቃ

ለቀድሞው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ለአሁኑ የአፍሪቃ ህብረት ምሥረታ ግንባር ቀደም ሚና በመጫውት ስሟ የሚነሳ ሃገር ናት ። ከዚያም ቀደም ሲል ሃገሪቱ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚታገሉ ሽምቅ ተዋጊዎችን በመደገፍ ለአፍሪቃ ከቅኝ ግዛት መላቀቅ ያደረገችው አስተዋጽኦም ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም ።

ኢትዮጵያ ፣ 50 አመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ ለሚገኘው ለቀድሞው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ለአሁኑ የአፍሪቃ ህብረት ምሥረታ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወተች ሃገር ናት ። ከዚያም ቀደም ሲል ሃገሪቱ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚታገሉ ሽምቅ ተዋጊዎችን በመደገፍ ክፍለ ዓለሚቱ ከቅኝ ግዛት እንድትላቀቅ ያበረከተችው አስተዋጽኦም ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም ። በዚህና ኢትዮጲያ አሁንም በአፍሪቃ ቀንድና በክፍለ ዓለሙ ባላት የጎላ ሚና ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናት ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ተካሂዶ ነበር ። በአመለካከቱ ለጀርመን ሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ የሚቀርበው ፍሬድሪሽ ኤበርት ሽቲፍቱንግ የተባለው የጀርመን ተቋም ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመሆን ባዘጋጀው በዚህ ዓውደ ጥናት ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic