የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጊዚያዊ ኮሚቴ | ኢትዮጵያ | DW | 02.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጊዚያዊ ኮሚቴ

«ነጻና እና ገለልተኛ እንዲሁም ኹሉንም ሙስሊም የሚወክል ጠንካራ ተቋም ይመስረት» የሚለው ጥያቄ ለዓመታት በርካቶችን ለእስር እና ለስደት ዳርጓል። ለዓመታት የዘለቀው ትግል ትናንት የኢትዮጵያ የዑለማዎች ምክር ቤት እና ጊዜያዊ የባለአደራ ኮሚቴን ለ6 ወራት በመሰየም ወደ አንድ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:11

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ እና አንድነት ሀገር አቀፍ ስበሰባ

«ነጻና እና ገለልተኛ እንዲሁም ኹሉንም ሙስሊም የሚወክል ጠንካራ ተቋም ይመስረት» የሚለው ጥያቄ ለዓመታት በርካቶችን ለእስር እና ለስደት ዳርጓል። ለዓመታት የዘለቀው ትግል ትናንት የኢትዮጵያ የዑለማዎች ምክር ቤት እና ጊዜያዊ የባለአደራ ኮሚቴን ለ6 ወራት በመሰየም ወደ አንድ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የትናንቱ ቀን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሙስሊሙ በጎሪጥ የሚተያይበት ችግር የተፈታበት መኾኑም ተገልጧል። 

ትናንት በጊዜያዊነት ለ 6 ወራት የተሰየሙት የኢትዮጵያ የዑለማዎች ምክር ቤት እና ጊዜያዊ የባለአደራ ኮሚቴ ከዚህ በፊት በየመስጅዱ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋል ተብሎ የታመነበት ውሳኔ ውጤት በመሁኑ እውነተኛ መፍትሄ እንደሚያመጣ እምነታቸው መሆኑን አንድ የቀድሞው መጅሊስ አባል ተናገሩ፡፡

በሌላ በኩል አሁን የተቋቋመው የኡለማዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው የተሰየሙት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ ትናንቱ ቀን ታሪካዊ አስደናቂ እና አስገራሚ ነበር፡፡ ከቅርብ አመታት ወዲህ በአመለካከት ችግር ሙስሊሙ በጎሪጥ እየተያየ ችግር ያለበት ሆኖ የቆየበት ጊዜ የተፈታበት ነው ብለዋል፡፡

የተሰየመው ጊዜያዊ አካልም የተለያየውን ህዝበ ሙስሊም ወደ አንድነት የሚያመጣና ትክክለኛውን እውነታ በማስተማር ወደ ህብረቱ የሚመልስ እንደሚሆን እናምናለን ይህም ለሃገር ፡ ለህዝብና ለመንግስት ከበድ ያለ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተቋቋመው አካል ከ 6 ወራት በኋላ የመጅሊሱን መሪዎች እንደሚያስመርጥም መነገሩ ይታወሳል።

ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች