የኢትዮጵያ መንግስት ማስተባበያ እና የአ.ብ.ነ.ግ መግለጫ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 1 2001ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር አ.ብ.ነ.ግ. በሰሜን ኦጋዴን ደገሀቡር አቅራቢያ በተዋጊዎቹ ና በኢትዮጵያ መንግስት ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው ሲል አስታውቋል ። በዚሁ መግለጫ ከረቡዕ የካቲት ሀያ አምስት ወዲህ በተካሄደው ውጊያ ሀያ አራት የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውና ፣ ስድስት የአካባቢው አርብቶ አደሮች በኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውም ተጠቅሷል ። ኦብነግ ሰሞኑን ደገሀቡር አቅራቢያ ተካሄደ ስላለው ውጊያ እና በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ላይ ደረሰ ስላለው ጥቃት ዶይቼቬለ የጠየቃቸው የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ዴታ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የተባለው ሁሉ ሀሰት ነው ብለዋል ።