የኢትዮጵያ መንግስት ለንቋሳነት «በከፍተኛ እየተባባሰ» መምጣቱ | ኢትዮጵያ | DW | 17.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግስት ለንቋሳነት «በከፍተኛ እየተባባሰ» መምጣቱ

መቀመጫዉን ዋሽግተን ዲሲ ያደረገዉ Fund for peace የተሰኘዉ ተቋም በሐገራት ሰላም፣ደንነትና ልማት ላይ ያተኮረዉን ዓመታዊ ዘገባዉን ሰኞ ዕለት ይፋ አድርጓል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:44

የመንግስት ለንቋሳነት

Fund for peace የተሰኘዉ ተቋም ጥናቱን ያደረገዉ በ12 አመላካቾች ወይም ጠቋሚዎች ላይ ተመስርቶ እንደሆነና መረጃዎችን ለመሰብሰብ አስፈላጊዉን ሳይንሳዊ ዘዴ እንደተጠቀመ የድርጅቱ የፕሮግራም ሐላፍ ሃናሃ ብላዝ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ከ12ቱ አመላካቾች ዉስጥ የሰበዓዊ መብትና ደንነት አያያዝ፣ የኢኮኖሚ እድገት፣ የሰዎች  መፈናቀልና መሰደድ፤ በየሐገራቱ ያለዉ የህግ ማዕቀፍ፣ ማሕበራዊ አጋልግሎትንና ጠቅላላ ብሶቶችን እንደሚያጠቃልልም ኃላፊዋ አብራርተዋል።

«ፍራጃይል ስቴት ኢንዴክስ» በተሰኘዉ ዓመታዊ ዘገባዉም ደቡብ ሱዳንን   በከፍተኛ ደረጃ ለጥፋት የተጋለጠች በማለት ከ178 ሐገራት አንደኛ ደረጃ ላይ  ሲያስቀምጣት፤ ኢትዮጵያ 15 ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለችበት ምክንያት የደሕንነትና የልማት ዋስትናዋ በጣም ለንቋሳ  በመሆኑ እና «እየተባባሰ» በመምጣቱ መሆኑን ዘገባዉ ይጠቅሳል።

«ላለፉት ዓመታት አመላካቾቹ በኢትዮጵያ በጣም እየተባባሱ ነዉ የመጡት። በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የነበሩ ተቃዉሞዎች የሰባዊ መብትና የሰዎች ደሕንነት አያያዝን አስከፊና እንዲባባስ አድርጎታል።  ላለፉት 10 ዓመታት ሰባዊ መብትና ደሕንነት ጉዳችን ጨምሮ የማሕበራዊ አገልግሎቶች በጣም መድከሙና የከተማና የገጠር ልማት መበላለጡ አንዱ ማሳያ ነዉ።»

የኢትዮጵያ መንግስት ሐገሪቱ ያለችበትን ደረጃ ለማሻሻል፤ የሰባዊ መብት ይዞታዎችን የማሻሻል ፖለትካዊ ፍቀደኝነት ሊኖረዉ ይገባል የሚሉት ዳይሬክተሯ የአሜርካ፣ የአዉሮጳና የሌሎች ለጋሽ ሐገሮችም ሚናም ከፍተኛ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።በገጥር ያሉት የጤና አጋልግሎት ተቋማትም መሻሻል እንዳለባቸዉ  አክለዉበታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በሰብአዊ መብትና በሕዝብ ደሕንነት ጥበቃ ላይ ያተኮሩ ይሕን መሠረል ዘገባዎችን የሚያወጡ ተቋማትን «ፀረ-ሰላም እና ፀረ-ልማት» ሲል ይወነጅላቸዋል።ብላዝ መንግሥት አጥኚ ተቋማትን ከሚወቅስ ይልቅ ችግሮቹን ለማሻሻል እንዲጥር ይመክራሉ።

«የኢትዮጵያ መንግስት በሐገሪቱ በአደጋ ጊዜ የሚከሰቱትን የሰባዓዊም ሆነ የደሕንነት ችግሮች በራሱ ለመቋቋም አቅም ማጎልበት እንዳለበት በጥብቅ አስስባለዉ። ሐገርቱ ተስፋ ሰጭ እቅዶች አሏት፣ የኦኮኖሚ እድገቱም አበራታች ነዉ። ግን በከተማና በገጠር ያለዉ ዕድገት  መመጣጠን አለበት።»

በዚህ ጉዳይ የአድማጮቻችንን አስተያየት ጠይቀን ነበር። በአማራ ክልል ነዋሪ ነኝ ያሉን ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ የሠብአዊ መብት ጥሰቱ ከዓመት ዓመት እየተባባሱ ነዉ የሚገኙት ይላሉ።

ዘገባዉ ለመገናኛ ዘዴዎች፤ ለፖሊሲ አዉጭዎች፣ ለእርዳታ ድርጅቶችና ለአጥኚዎች እንደ ግበዓት ይጠቅማል ሲሉ ሃና ብላዝ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ፅፌት ቤት ኃላፊዎች የመንግሥትን አቋም እንዲያስረዱን ያደርግነዉ ሙከራ አልተሳካም።


መርጋ ዮናስ
ነጋሽ መሐመድ 


          


 

Audios and videos on the topic