የኢትዮጵያ መንግስትና አምነስቲ ኢንተርናሽናል | ኢትዮጵያ | DW | 13.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግስትና አምነስቲ ኢንተርናሽናል

የኢትዮጵያ መንግስት የደነገገው ህግ የሰብዓዊ መብት ስራን ክፉኛ መገደቡን አለም አቀፍ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት -አምንስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት ባወጣው ዘገባ ገልጿል። ዘገባው የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው ህግ በአሻሚ ቃላት የተሞላ ነው ይህም መብት የማስከበሩን ስራ አስተጓጉሏል።

አለም አቀፉ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት -አምንስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የደነገገው ህግ የሰብዓዊ መብት ስራን ክፉኛ የገደበ ነው።

የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳይ ምክትል ዳሬክተር - ሚሻኤለ ካጋሪ የትኛውን ህግ ማመላከታቸው እንደሆነ ሲያብራሩ  « የተመለከትነው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የማህበራቱን አዋጅ ነው። ህጉ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የማህበራት ተቋማት ላይ ያልተለመደ አስገዳጅ የአሰራር ሁኔታ በሲቪል ማህበራቱ ላይ ይጥላል። በአዋጁ የተቋቋሙ የበጎ አድራጎትና የማህበራት መስሪያ ቤት የግብረ ሰናይ ተቋማትን ሐብት ንብረት ማገድ ይችላል። ለሌሎች ተመሳሳይ አላማ አላቸው ለሚባሉ ለሌሎች ድርጅቶች ማስተላለፍ ይችላል፣የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የፈለጉትን ሰነድ እና መረጃ የማየት እና የመመርመር መብት አላቸው። ህጉ ራሱ የገንዘብ ምንጭን ይገድባል።»

ይህም  አንድ ግብረ ሠናይ ድርጅት ከ10 ከመቶ በላይ የሚሆን ስራ ማስኬጃ ከውጭ አገር ድጎማ ማግኘት አይፈቀድለትም። 90 ከመቶው ከአገር ውስጥ መሆን ይገባዋል የሚል ነው። ይህ መመሪያ ደግሞ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ስራ አጓቷል ይላሉ ዳሬክተሯ።« ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳስብ ነው። የሰብዓዊ መብት ስራዎች አስፈላጊነታቸው የመንግስትን ፖሊሲ እና ትግበራትን ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ተራ ኢትዮጵያዊ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ የሴቶችን መብት ወይም ጎጂ ልማድ ስራዎችን መመልከት ይቻላል።»

Gebriemeskel, carrying water, before project took 3 hours to water point, now only 15 mins. Tigray, Ethiopia am 6.7.2009 fotografiert im Feb 2011 geladen Lizenz: http://creativecommons.org/licenses/by-nc-sa/2.0/deed.de +++CC/waterdotorg+++

የአምንስቲ ኢንተርናሽናልን ወቀሳ በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ስምኦን  ወቀሳዉን አልተቀበሉትም። አቶ በረከት ለፈረንሳይ የዜና ወኪል- አዣንስ ፍራንስ ፕሪስ እንደነገሩት የአምኒስቲ መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የተቃጣ ዘመቻ ነዉ። ህጉ የሲቪክ ማህበረሰብን ለመዝጋት ያለመ አይደለም፥ በተቃራኒዉ ህግን ተከትሎ ለሚሰሩ የሚረዳ ነዉ ብለዋል።

የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳይ ምክትል ዳሬክተር - ሚሻኤለ ካጋሪ ግን በዚህ አይስማሙም። እንደውም በህጉ ምክንያት የኢትዮጵያ ህዝብ ለገለልተኛ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች በመቅረብ ችግሩን መግለፅ አልቻለም። ስለዚህ ይህ ዘገባ አስፈላጊ ነበር።

«ዘገባው የወጣው ምን እየተደረ እንደሆነ ለማጋለጥ ነው። ምክንያቱም የኢትዮጵያ መንግስት የህጉ አላማ  የሲቪልማህበረሰበራትን ስርዕት ማስከበር ነው ሲል በፊትም አሁንም ደጋግሞ ይናገራል። አምንስቲ ኢንተርናሽናል  የሲቪልማህበረራት መተዳደሪያ ደንቦች እንደሚያስፈልጋቸው ይቀበላል። ሆኖም ህጉየሲቪሉንማህበራትን ስርዕት እያስከበረ አይደለም። የሰብዓዊ መብት ተግባራትን እየገደለ እንጂ! »

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 13.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14Jbb
 • ቀን 13.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14Jbb