የኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃና ተቃዋሚዎች | ኢትዮጵያ | DW | 27.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

 የኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃና ተቃዋሚዎች

ሰዎችን ከማሰር እንቅስቃሴ፤ ንግግር፤ ግንኙነታቸዉን እስከ መግታት፤ የመገናኛ ዘዴዎችን ሥርጭትና ወይም ኅትመት ከመዝጋት፤ የኢንተርኔት አገልግሎትን እስከማቋረጠዉ የደረሰዉ እርምጃ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሀገሪቱን ለማረጋጋት ጠቅሟል።ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፤ የመብት ተሟጋቾች እና ገለልተኛ ታዛቢዎች ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:47
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:47 ደቂቃ

የመንግሥት እርምጃና ተቃዋሚዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈዉ መስከረም ማብቂያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ ወዲሕ የወሰዳቸዉ እርምጃዎችም ሆኑ የባለሥልጣናት ሹም ሽር ለማድረግ ማቀዱ የሕዝቡን ጥያቄ እንደማይመልስ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና ሙሑራን አስታወቁ። መንግሥት የሚቃወሙ ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ አዋቂዎች እንደሚሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኢትዮጵያን ወታደራዊ አገዛዝ ሥር ያዋለ ነዉ። እነሱ እንደሚሉትም በአዋጁ መሠረት የተወሰዱት እርምጃዎችም ሆኑ የታቀደዉ ሹም ሽርም የበለጠ አፈናን ከማስፈኑ በስተቀር የሕዝብ ጥያቄን አይመልስም። ነጋሽ መሐመድ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈዉ መስከረም ማብቂያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ ወዲሕ በተለያዩ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸዉን በሺሕ የሚቆጠሩ ተጠርጣሪዎች ማሰሩን፤ ሌሎች እጃቸዉን መስጠታቸዉን፤ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መማረኩን በተደጋጋሚ አስታዉቋል። ሰዎችን ከማሰር እንቅስቃሴ፤ ንግግር፤ ግንኙነታቸዉን እስከ መግታት፤ የመገናኛ ዘዴዎችን ሥርጭትና ወይም ኅትመት ከመዝጋት፤ የኢንተርኔት አገልግሎትን እስከማቋረጠዉ የደረሰዉ እርምጃ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሀገሪቱን ለማረጋጋት ጠቅሟል።
ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፤ የመብት ተሟጋቾች እና ገለልተኛ ታዛቢዎች ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት። የቀድሞዉ የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አንጋፋ ታጋይ አቶ አስገደ ገብረ ሥላሴ አንዱ ናቸዉ።
                          
የቀድሞዉ ብቸኛዉ የተቃዋሚ ፓርቲ የምክር ቤት እንደራሴ አቶ ግርማ ሰይፉ ያክሉበታል።የፍልስፍና ፕሮፌሰር ዶክተር ዳኛቸዉ አሰፋ በበኩላቸዉ አዋጁ ከማርሽል (የጦር) ሕግ አይለይም ባይ ናቸዉ። ለተነሱት ጥያቄዎች መንግሥት የወሰደና የሚወስዳቸዉ እርምጃዎችም ዶክተር ዳኛቸዉ

እንደሚያምኑት ወታደራዊ መንገድ መሆናቸዉን ጠቋሚ ነዉ።
                                      
መንግሥት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት ከወሰዳቸዉ እርምጃዎች በተጨማሪ በቅርቡ የፌደራሉን መንግሥት የካቢኔ አባላትን ሽሮ-ሌሎች እንደሚሾም አስታዉቋል። አቶ ግርማ ሰይፉ «ዕቃን ጨለማ ዉስጥ ጥሎ መብራት ያለበት ሌላ ሥፍራ መፈለግ» ዓይነት ይሉታል።
                                      
አቶ አስገደ ለዉጥ አያመጣም ባይ ናቸዉ።
                      
ዶክተር ዳኛቸዉ እስኪ እናያለን።
                 
ዉስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚሉት የየክልል መስተዳድሮች የየራሳቸዉን ሹም ሽር ካደረጉ በኋላ የፌደራሉ መንግሥት ሹም ሽር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ


 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች