የኢትዮጵያ መንግሥት መርሕ ና አዲሱ ዓመት | ኢትዮጵያ | DW | 12.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግሥት መርሕ ና አዲሱ ዓመት

ናይሮቢ-ኬንያ ዉስጥ በስማበለዉ ይደረጋል የተባለዉ ድርድር ሒደት እስካሁን ግልፅ አይደለም።ይሁንና ድርድሩ ከእስረኞቹ መለቀቅ ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በተቃዋሚዎቹ ላይ የያዘዉን አክራሪ አቋም የማለሳለሱ ምልክት ነዉ-አይደለም የሚል ክርክር ማስነሳቱ አልቀርም።

***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).*** DW-Grafik: Per Sander 2011_03_10_Laender_Prio_A_B

የኢትዮጵያ መንግሥት ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ባገባደደዉ አዲስ ዓመት ዋዜማ ከአንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ በላይ እስረኞችን በይቅርታ ለቅቋል።መንግሥት ከዚሕም በተጨማሪ የሐገሪቱ ምክር ቤት ሐቻምና ባሸባሪነት ከፈረጃቸዉ ሠወስት የሐገር ዉስጥ የፖለቲካ ድርጅቶች መካካል ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦብነግ) ለመደራደርም ተስማምቷል።ናይሮቢ-ኬንያ ዉስጥ በስማበለዉ ይደረጋል የተባለዉ ድርድር ሒደት እስካሁን ግልፅ አይደለም።ይሁንና ድርድሩ ከእስረኞቹ መለቀቅ ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በተቃዋሚዎቹ ላይ የያዘዉን አክራሪ አቋም የማለሳለሱ ምልክት ነዉ-አይደለም የሚል ክርክር ማስነሳቱ አልቀርም።ገመቹ በቀለ በዚሕ ጉዳይ ላይ ሁለት የፖለቲካ ተንታኞችን አነጋግሮ ያጠናቀረዉ ዘገባ አለ።

ገመቹ በቀለ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic