የኢትዮጵያ መንግሥት መርሕና የገጠመዉ ተቃዉሞ | ኢትዮጵያ | DW | 23.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግሥት መርሕና የገጠመዉ ተቃዉሞ

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚዎቹን ያንገላታል፥ የሰብአዊ መብት አያከብርም፥ መልካም አስተዳደርን አይከተልም የሚለዉ ወቀሳና ትችት እየተደጋጋመ ነዉ።

default

እዚሕ አዉሮጳ የሚገኙ የመብት ተሟጋቾች እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ ከ1997ቱ ምርጫ ወዲሕ በተቃዋሚ ፖለቲከኞች፥መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማትና በጋዜጠኞች ላይ የሚፈፅመዉ በደል እየተባባሰ ነዉ። ምዕራባዉያን ሐገራት ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጡትን ርዳታና ድጋፍ እንዲያቆሙ የሚጠይቁ ወገኖችም አሉ።ሉድገር ሻዶምስኪ ያጠናቀረዉን ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ተርጉሞታል።

ከአዲስ አበባም በደረሰን ዘገባ መሠረት ሁለት የኦሮሞ ህዝብን የወከሉ ፓርቲዎች በርካታ አባሎቻችን በገዢዉ ፓርቲና በፓሊስ ኃይሎች እየታሰሩብነዉ ሲሉ ክስ አሰምተዋል። ኦፍዲንና ኦብኮ 412 አባሎቻቸዉ መታሰራቸዉን ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታዉቀዋል። የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸዉ ድርጊቱ አልተፈፀመም ሲሉ አስተባብለዋል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ ታደሰ እንግዳዉ/ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ