የኢትዮጵያ መንግሥትና የአዉሮጳ ሕብረት | ኢትዮጵያ | DW | 31.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግሥትና የአዉሮጳ ሕብረት

የኢትዮጵያ ጉዳይ ልዑክ ባወጣዉ መግለጫ የእስረኞቹ አያያዝ የኢትዮጵያን ሕገ-መንግሥት፤ ዓለም አቀፍና አሐጉራዊ የሠብአዊ መብት ድንጋጋዎችን ያከበረ ለመሆኑ ማረጋገጫ እንዲሰጠዉም አሳስቧል።እስረኞቹ ከቤተ-ሠቦቻቸዉ፤ ከዘመድ ወዳጆቻቸዉ እና ከጠበቆቻቸዉ ጋር እንዲገናኙ፤ የዋስ መብታቸዉ እንዲከበር እና የፍርድ ሒደቱም ግልፅና ነፃ እንዲሆን አሳስቧልም

የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን፤የአምደ-መረብ ፀሐፍትንና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ማሰሩ እንዳሳሰበዉ የአዉሮጳ ሕብረት አስታወቀ።በሕብረቱ የኢትዮጵያ ጉዳይ ልዑክ ባወጣዉ መግለጫ የእስረኞቹ አያያዝ የኢትዮጵያን ሕገ-መንግሥት፤ ዓለም አቀፍና አሐጉራዊ የሠብአዊ መብት ድንጋጋዎችን ያከበረ ለመሆኑ ማረጋገጫ እንዲሰጠዉም አሳስቧል።እስረኞቹ ከቤተ-ሠቦቻቸዉ፤ ከዘመድ ወዳጆቻቸዉ እና ከጠበቆቻቸዉ ጋር እንዲገናኙ፤ የዋስ መብታቸዉ እንዲከበር እና የፍርድ ሒደቱም ግልፅና ነፃ እንዲሆን አሳስቧልም።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic