የኢትዮጵያ መንግሥትና አምንስቲ ኢንተርናሽናል | ዓለም | DW | 02.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኢትዮጵያ መንግሥትና አምንስቲ ኢንተርናሽናል

ኢትዮጵያን እንዲለቁ ከተነገራቸዉ አንዷ ክሌር በስተን እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ የገቡት በተለያዩ መስተዳድሮች ያለዉን የሰብአዊ መብት ይዞታ ለአስራ-ሁለት ቀን ለማጥናት ነበር።አዲስ አበባ በደረሱ በሰወስተኛዉ ቀን ግን ከሐገር እንዲወጡ ተነግሯቸዋል

default

የኢትዮጵያ መንግሥት የአለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የየአምንስቲ ኢንተርናሽናል ሁለት አጥኚዎችን ማባረሩን ድርጅቱ «አሳዛኝ» አለዉ።ኢትዮጵያን እንዲለቁ ከተነገራቸዉ አንዷ ክሌር በስተን እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ የገቡት በተለያዩ መስተዳድሮች ያለዉን የሰብአዊ መብት ይዞታ ለአስራ-ሁለት ቀን ለማጥናት ነበር።አዲስ አበባ በደረሱ በሰወስተኛዉ ቀን ግን ከሐገር እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ግን ሁለቱ ሰዎች ከኢትዮጵያ የወጡት ሥራቸዉን አጠናቀዉ ነዉ ይላሉ።አምንስቲ ኢንተርናሽናል ከባልደረቦቹ ጋር በመነጋገራቸዉ ታስረዋል ያላቸዉ ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናት ባስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋልም።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic