የኢትዮጵያ መብራት ኃይልና ፕሮጀክቶቹ | ኢትዮጵያ | DW | 14.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መብራት ኃይልና ፕሮጀክቶቹ

ግንባታው የተጀመረውን የህዳሴ ግድብ ጨምሮ በአባይ ወንዝ ላይ አራት ግድቦችን ለማሠራት ጥናቶች እየተጠናቀቁ መሆኑን የኢትዮጵያ መብራት ኃይል አስታወቀ ።

default

ድርጅቱ በመንግሥት የሚገነቡትን ከፍተኛ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ለማሠራት ከ 8 ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች ጋር ባለፈው ሳምንት ስምምነት ተፈራርሟል ። የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ለኃይል ማመንጫ መሰረተ ልማት የሚወጣውን ገንዘብ በማባከንና በብልሹ አሠራር በሃገሪቱ ጠቅላይ ኦዲተር ከዚህ ቀደም ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለዚሁ ዶቼቬለ የጠየቃቸው የመብራት ኃይል ስራ አስኪያጅ አቶ ምህረት ደበበ መስሪያ ቤታቸው ወደፊት ሊያሰራቸው በተፈራረማቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ስህተቶቹን ለማረም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።ታደሰ እንግዳው

ታደሰ እንግዳው

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic