የኢትዮጵያው የምርጫ ዝግጅትና፣ የአውሮፓው ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች መሪ፣ | ኢትዮጵያ | DW | 14.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያው የምርጫ ዝግጅትና፣ የአውሮፓው ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች መሪ፣

የአውሮፓው ኅብረት ፣ የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ምርጫ ለመታዘብ 150 ልዑካን የሚያሠማራ ሲሆን፣ 90 ገደማ የሚሆኑት የቅድመ-ምርጫውን ሂደት ለመከታተል ከተላኩ ቆይቷል።

default

ቀሪዎቹ፣ ምርጫው ሊጀመር አቅራቢያ ወደዚያ ይጓዛሉ። የ 150 ው ታዛቢ ልዑካን መሪ፤ ኔደርላንዳዊው የአውሮፓ ኅብረት አባል ታይስ በርማን ደግሞ የፊታችን ሰኞ ይሆናል አዲስ አበባ የሚገቡት። የብራሰልሱ ዘጋቢአችን ፣ ገበያው ንጉሤ፣ ክግራና ከቀኝ እየተሰነዘሩ ስላሉ ወቀሳዎች ከአንድ እጩ ተወዳዳሪ ጋር በጠቅላላ 4 የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ እንዲሁም አንድ ፖሊስ ስለመገደላቸው መገለጡ፣ የፈጠረውን የፖለቲካ ውጥረትና አሳሳቢነት፣ ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም በማንሣት አነጋግሮአቸዋል።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ