የኢትዮጵያውያን የልደት በዓል አከባበር | ኢትዮጵያ | DW | 07.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያውያን የልደት በዓል አከባበር

የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ዛሬ ታህሳስ ሀያ ዘጠኝ እያከበሩ ነው።

default


1)
ይኸው ዕለትም ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ በመከበር ላይ ይገኛል። በዓሉ በድሬዳዋ ከተማ እና ባካባቢዋ በክርስትና እምነት ተከታዮች ሞቅ ደመቅ ባለ መልኩ እየተከበረ ነው። የድሬዳዋ ወኪላችን ስለ በዓሉ አከባበር በከተማይቱ በመዘዋወር የህዝብ አስተያት አሰባስቦዋል። የበዓሉን ዝግጅት ለመቃኘትም ትናንት በዋዜማው አሸዋ እየተባለ በሚጠራው የፍየሎች፡ የከብቶች መሸጫ የገበያ ቦታ እና ወደ ታላቁ የገበያ ማዕከል ቀፊራ ተዘዋውሮ ነበር።


2)
በሳውዲ ዐረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የልደትን በዓል አክብረዋል። ብዙዎቹ የገናን በዓል የመሳሰሉ የሀይማኖት በዓሎች በጋራ እንደሚያከብሩ የጄዳው ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ ዘገባ ያመለክታል። በጄዳ ያሉት አበሾች ለበዓሉ የሚያደርጉትን ዝግጅትና በዓሉንም እንዴት እንደሚያከብሩት ነቢዩ ወደ ገበያ ወጣ በማለት አንዳንዶችን አነጋግሮ ዋል።


3)

የልደት በዓል በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላ ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውንም ዘንድ በሀገር ወግና ልምድ መሰረት በመከበር ላይ ይገኛል። እንደሚታወሰው በውጭ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በየሚኖሩባቸው ሀገሮች ከአስራ አምስት ቀናት በፊት የፈረንጆቹን የገናን በዓል ፡ ከአንድ ሳምንት በፊት ደግሞ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት አክብረዋል። የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ስለበዓሉ ያነጋገራቸው አንዳንድ ኢትዮጵያውያን፡ የገናን በዓል ሁለቴ የሚያከብሩበት ሁኔታ ይህ በዓላቱን ሁለቴ ማክበሩ ምን ተጽዕኖ አሳርፎባቸዋል።

4)

የልደት በዓል ዛሬ በተከበረባት ኤርትራም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ አራተኛ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያለው ለሌለው እንዲያካፍል ጥሪ አቅርበዋል። የተመድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ከጥቂት ጊዜ በፊት ማዕቀብ የጣለባት የኤርትራ ህዝብ የልደት በዓል አከባበርን በተመለከተ ወኪላችን ጎይትኦም ቢሆን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ዩሀንስ ገብረእግዚአብሄር/ጎይትኦም ቢሆን/ነቢዩ ሲራክ/አበበ ፈለቀ

አሪያም ተክሌ

Audios and videos on the topic