የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በሽሜሲ | ኢትዮጵያ | DW | 09.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በሽሜሲ

መኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸው ፣ በሀሃጅና ኡምራ ፣ እንዲሁም በባህር ገብተው ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎች ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ መንግስት ባደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡ በርካቶች ናቸው። ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት የሳዑዲ አረቢያ ሽሜሲ መጠለያ ውስጥ መጠነኛ ሁከት ተቀስቅሶ ነበር።

መኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸው ፣ በሀሃጅና ኡምራ ፣ እንዲሁም በባህር ገብተው ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎች ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ መንግስት ባደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡ በርካቶች ናቸው። ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት የሳዑዲ አረቢያ ሽሜሲ መጠለያ ውስጥ መጠነኛ ሁከት ተቀስቅሶ ነበር።እጃቸውን ሰጥተው በሽሜሲ መጠለያ ከአንድ ወር ላላነሰ ለቆዩትና ሰነዳችሁ ተሟልቷል ለተባሉት አውሮፕላን ባለመቅረቡ እና ከ45 ኪሎ በላይ እቃ አይፈቀድም በመባሉ በተፈጠረ መጉላላት ከትናንት በስትያ ከቀትር በኋላ መጠነኛ ሁከት ቀስቅሶ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል። የሣዑዲ አረቢያው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ነብዩ ሲራክ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic