የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሞት በካሌ ፈረንሳይ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 28.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሞት በካሌ ፈረንሳይ

ባሳለፈነው የካቲት ና በያዝነው የመጋቢት ወር ኢትዮጵያውያንና የሌሎች አገራት ስደተኞች በካሌ በተለያዩ አደጋዎችና ባልታወቁ ምክንያቶች ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡

ፈረንሣይን በስተሰሜን ከእንግሊዝ የምታዋሰነው የካሌ ደሴት ስደተኞች ወደ ታላቅ ብሪታንያ ለመግባት እንደ መሸጋገሪያ የሚጠቀሙባት የወደብ ከተማ ናት፡፡ በዚህች ወደብ በኩል ሰደተኞች በምግብ፣ በአልባሳት በቁሳቁስ መጫኛ ካሚዮኖች ተደበቀው ያለጋዊ የጉዞ ሰነድ ወደ እንግሊዝ ለመሻገር ይሞክራሉ። ከጊዜ ወደ ግዜ የሁለቱ አገራት ደንበር ጠባቂ ፖሊሶች ጥብቅ ክትትላቸውን ቢያጠነክሩም አሁንም በርካታ ሰደተኞች በአደገኛ ጉዞ ድንበር ለማቀረጥ ሲሞክሩ ሕይወታቸውን የሚያጡበት አጋጣሚ በርካታ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ባሳለፈነው የካቲት በያዝነው የመጋቢት ወር ኢትዮጵያውያንና የሌሎች አገራት ስደተኞች በካሌ በተለያዩ አደጋዎችና ባልታወቁ ምክንያቶች ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡ ከዚህ ቀደም ወደ እንግሊዝ በሚያሻግረው መሿለኪያ አቅራቢያ ይገኝ የነበረው የሳንጋት የሰደተኞች መቀቢያ ጣቢያ ..አ በ2002 ከተዘጋ በኋላ በአካባቢው ቃሚ የስደተኞች መቀበያ ጣቢያ አለመኖር የሰደተኞችን ሕይወት አስቸጋሪ እንዳደረገው ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ገልፀዋል ።ዝርዝሩን ሃይማኖት ጥሩነህ ከፓሪስ ልካልናለች

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic