የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጥያቄና“Control Risks” | ኢትዮጵያ | DW | 11.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጥያቄና“Control Risks”

ሮይተርስ ዜና አገልግሎት፣ ትናንት ማታ ከአዲስ አበባ ባቀረበው ዘገባ ላይ ፤ካለፈው ጥር ወር አንስቶ ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ከሞላ ጎደል በየሳምንቱ በየመሥጊዱ ተቃውሚ ሲሰማ ቆይቷል ። መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል የሚል ተቃውሞ የሚያሰሙት

default

ሙስሊሞች፣    የሃይማኖት አስተምህሮትን ከሚያጠብቀው ከሳላፊስት ይልቅ ለዘብ ያለውን የሱፊ አስተምህሮትና እሴቶች የሚከተሉ መሆናቸውን ነው የሚገልጹት። በሰላማዊ መንገድ ጥያቄአቸውን ያቀረቡት፤ ምላሽ እስኪያገኙ የሚገፉበት መሆናቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ነው። ዋና ጽ/ቤቱ በለንደን የሚገኘው Control Risks ዓለም አቀፍ ድርጅት ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞው ከቀጠለ ጠጣር እርምጃ ይወስድ ይሆናል ሲል አስተያየት ሰንዝሯል። ስለአንዴትነቱ ተክሌ የኋላ፤ የድርጅቱን የውዝግቦች ጉዳይ ተንታኝ ምስተር ፓትሪክ ሜየርን በስልክ  አነጋግ ሮአቸዋል።

Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Flash-Galerie

በተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን በሰው ሠራሽ ችግሮች ከሚመሠቃቀለው የአፍሪቃ ክፍል አንዱ የአፍሪቃው ቀንድ ነው። የፖለቲካና  የኤኮኖሚ ችግሮች፣ ሃይማኖታዊ አክራሪነትን እስከመጋበዝ ለመድረሳቸው ሶማልያ ምሳሌ ናት። በመጀመሪያ ድርጅታቸው ባለፉት ወራት ፤ በኢትዮጵያና ባካባቢው ስለታዘበው ያወሱልን ዘንድ ነበረ ፣ ምስተር ፓትሪክ ማዬርን የጠየቅኳቸው።

«ኢትዮጵያ ፤ በአፍሪቃ ቀንድ አክራሪ እስልምናን በመቋቋም ረገድ፣ የምዕራቡ ዓለም ተጓዳኝ ናት። ይህን በማከናወን ረገድ በተለይ በሶማልያ መሪ ሚና ነው ያላት። በዚያም በተለይ በደቡብና በማዕከላዊው ሶማልያ እስላማዊ አክራሪነትን ለመታገል በወታደራዊ ኃይል ጣልቃ እስከመግባት ደርሳለች።

በቅርቡም፤ ኬንያንና የአፍሪቃን ኅብረት ከመሳሰሉ ተጓዳኞች ጋር በመሰለፍ ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያለውን አክራሪ ድርጅት አሸባብን ለመውጋት ተሠማርታለች። ኢትዮጵያ፣ የምዕራቡ ጠንካራ ተጓዳኝ  ሆና ቆይታለች። ወደፊትም ፤ እንደሚመስለኝ፣ በዚህ መልኩ ትቀጥላለች።»

Gambia Street in Addis Abeba, Äthiopien

የምዕራቡ ተጓዳኝ የሆነ አገር፣ የምዕራቡን እሴቶችም መቀበል ይኖርበታል ብለው የሚያስቡ አሉ። በኢትዮጵያ  ዴሞክራሲ የለም፤ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደቀጠለ ነው፤ የፕረስ ነጻነት ከባድ ፈተና ላይ ወድቋል እያሉ የሚጽፉ፤ የሚያሰሙ፤ መገናኛ ብዙኀን  አሉ። በእንዲህ  ሁኔታ፤ እንዴት ነው የምዕራቡ ተጓዳኝ ሆና የምትቀጥለው?

«ከምዕራባውያን መንግሥታትና ተቋማት፣ ኢትዮጵያ የውስጣዊ አስተዳደሯን ጉዳይ እንድታስተካክል ግፊት ቢኖርም፣ ተጨባጩ ሁኔታ እንደሚያሳየን፤ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች፤ በተለይ ዩናይትድ እስቴትስን የመሳሰሉ አገሮች በአፍሪቃው  ቀንድ  የአሸባሪነት ሥጋትን በተመለከተ ነው ትኩረት የሚያደርጉት»።

የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ፤ ጥያቄ ባቀረቡም ሆነ ተቃውሞ ባሰሙ ሙስሊሞች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ ይወስድ ይሆናል ሲል ፣ ድርጅትዎ፣   ምን ማለቱ ነው?

«ኢትዮጵያ፣  በእርግጥ የክርስቲያኖች አገር ብቻ አይደለችም፤ በዛ ያሉ ሙስሊሞችም የሚኖሩባት አገር ናት። እርግጥ ነው፤ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ፤ የኢትዮጵያ  መንግሥት የሚወስደው እርምጃ እንደሚያሳስበው የታወቀ ነው። መንግሥት በሚቃወሙት ላይ ምን ያደርጋል? በተቃውሞው ነጥቦችም ሆነ ቅሬታዎች ፤ በእነዚህ ዝርዝር ጉዳዮች አስተያየት ከመስጠት ብቆጠብ እመርጣለሁ።»

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

 • ቀን 11.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14u8u
 • ቀን 11.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14u8u