የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ስብሰባ በፍርንክፈርት | ኢትዮጵያ | DW | 04.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ስብሰባ በፍርንክፈርት

ጀርመን ውስጥ፤ «የኢትዮጵያውያን የውይይትና ትብብር መድረክ» የተሰኘው ማሕበር ባለፈው ቅዳሜ ፤ ፍርንክፈርት ላይ ባዘጋጀው ጉባዔ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፣ ወንዶችና ሴቶች ተሳትፈዋል። ሁለት ታዋቂ እንግዶች በስብሰባው በመገኘት ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ፣ግጥሞች ተነበዋል።

የስብሰባው ሥርዓት የተከፈተው በቅርቡ በሊቢያ፤ በደቡብ አፍሪቃና በየመን በአሠቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን የሕሊና ጸሎት በማድረግ ነው። ንግግር ያሰሙት ተጋባዥ እንግዶች፤ ኢትዮጵያውያን በዓለም ዙሪያ ፤ ወዳጆች፤ አጋዦች እንደሌላቸው በአጽንዖት ከማስገንዘባቸውም፤ ወቅቱ፤ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፣ ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ ፤ በአንድነት፣ በፍቅር እንዲቆሙ የሚገፋፋ አማራጭ የሌለው ዐቢይ ጉዳይ ነው ብለዋል። በስብሰባው ተገኝቶ የነበረው ጎይቶም ቢሆን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጎይቶም ቢሆን

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic