የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ይዞታ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 17.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ይዞታ

ሰሜን አፍሪቃዊቷ አገር ሊቢያ የጦርነት አውድማ ከሆነች ወዲህ በርካታ የውጭ ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ከሊቢያ ሸሽተው ወጥተዋል ።

default

ብዙዎቹ ወደ ጎረቤት ሀገራት ግብፅ እና ቱኒዝያ የሄዱ ሲሆን ፤ እድል ቀንቷቸው ከአስቸጋሪው ሁኔታ ያመለጡት በሺህዎች የሚቆጠሩት ደግሞ የሜዲቴራንያንን ባህር በጀልባዎች አቋርጠው ወደ ኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ እና ወደ ሌሌላኛ ደሴት ማልታ መግባት ችለዋል ።ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ደግሞ በጉዞ ላይ የውሐ ሲሳይ ሆነው መቅረታቸው በየጊዜው እየተዘገበ ነው ። ከአደገኛ የባህር ላዩ ጉዞ ተርፈው ወደ ነዚህ ደሴቶች ከገቡት ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ይገኙበታል ። እነዚህ ስደተኞች በደረሰቡቸው የአውሮፓ አገራት በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ? የወደፊቱስ እጣቸው ምን ይሆን ? የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

ሒሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic