የኢትዮጵያዉያን የባህል እና የፖለቲካ መቻቻል እንዴት ይታያል? | ባህል | DW | 10.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የኢትዮጵያዉያን የባህል እና የፖለቲካ መቻቻል እንዴት ይታያል?

ዛሬ ዛሬ ታሪክ ሆኖ ሊነገር የቀደሙት ኢትዮጵያዉያን ለጋራ ጉዳይ በጋራ ይቆሙ የነበረዉ በመካከላቸዉ ልዩነትም ሆነ ቅሬታ ሳይኖር ቀርቶ ሳይሆን በመቻቻል ባህላቸዉ ተሳስረዉ እንደሆነ ይነገራል።

መቻቻል ወይም ማስተዋል የዛሪን ሳይሆን የነገን የማለም፤ ከምንም በላይ ራስን የመግዛት ነፀብራቅ መሆኑ ብዙዎች ይስማሙበታል። ይህ ደግሞ ከዉስጡ ከተገኙበት ማህበረሰብ ብሎም ካደጉበት፣ ከጎለመሱበት ሊቀዳ እንደሚችል ይገመታል። ኢትዮጵያዉያን ትሁትነት፣ ታጋሽነት፣ እንግዳ ተቀባይነት በብዙ ጸሃፊዎች ይጠቀሳል። ይህ ታጋሽነት እና ትህት እስከ ምን ደረስ ተብሎ ሲፈተሽ ደግሞ  በተለይ እርስ በርስ ባለ ግንኙነት ላይ ጥያቄ የሚያስነሱ ክስተቶች ሲያጋጥም ይስተዋላል። የመቻቻል ባህል በተለይ ብዙዎች እንደሚሉት ከ60ዎቹ ወዲህ ባለዉ ትዉልድ እየተሸረሸረ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

Blick auf ein Graffiti mit den Worten Safety und Freedom (Sicherheit und Freiheit) in den Schalen einer Waage, aufgenommen am 26.02.2009 in Erfurt. Foto: Arno Burgi +++(c) dpa - Report+++

መንግስት ተቃዋሚዎቹን የሚይዝበት እና መገናኛ ብዙሃን ላይ የሚወስደዉ ርምጃ ሲታይ፤ በአንፃሩ ተቃዋሚዎች አፀፋ። ከተለያዩ ድረ ገፆች የሚነበቡ ፅሁፎችም ለዚህ ማሳያ ይጠቀሳሉ። ግለሰቦች የወጡበት ኅብረተሰብና ባህል ነፀብራቅ ናቸዉከተባለ፤ የኢትዮጵያዉያን የባህል እና የፖለቲካ መቻቻል እንዴት ይታያል? በያዝነዉ ሳምንት ዶይቼ ቬለ ሶስት እንግዶችን ጋብዞ አወያይቷል። በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆኑት የስነ-ልቦና እና የስነ-አዕምሮ ባለሞያ፤ ወ/ሮ አበባ ፈቃደ፤ በአዳማ ነዋሪ የሆኑት እና በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ለአስራ አምስት አመት አገልግለዉ በጥሩታ ላይ የሚገኙት የህብረተሰብ ጉዳይ ጥናት ምሁሩ ዶ/ር ገመቹ መገርሳ፤ እንዲሁም በአፍሪቃ ህብረት ጉዳዮች ላይ አማካሪ የሆኑት አቶ መሃሪ ታደለ ናቸዉ። ሙሉዉን ዉይይት ያድምጡ!


ሸዋዪ ለገሰ
አዜብ ታደሰ  

Audios and videos on the topic