የኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ጩኸት | ኢትዮጵያ | DW | 14.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ጩኸት

በሌሎች ሐገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተበደልን ነዉ ይሉ ይዘዋል።ስደተኞቹ እንደሚሉት የየሐገሩ ባለሥልጣናት ያስሯቸዋል፥ ያንገላቷቸዋል፥ ያስፈራሯቸዋል፥ ቀለል ሲል ደግሞ ጉቦ ይጠይቋቸዋል።በየሥፍራዉ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ለዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች በየጊዜዉ አቤት ቢሉም እስካሁን የረዳቸዉ የለም

In this photo taken Tuesday, June 26, 2012, Tanzanian officials note down details from some of the seventy survivors of an incident where over forty others suffocated to death in a truck container near Chitego Forest, about 130km (80 miles) east of the capital Dodoma, in Tanzania. An official in Tanzania says that 43 Ethiopian and Somali nationals suffocated in the truck they were being smuggled in and Tanzania's state television said the bodies were thrown off the truck and dumped in the bush after the driver of the truck realized some of the people he was smuggling had perished. Tanzania lies on a smuggling route Africans use to travel to South Africa, where there are more economic opportunities.(Foto:AP/dapd)

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች አምና-ታንዛኒያ

የሳዑዲ አረቢያ ፀጥታ አስከባሪዎችና ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ይተባበራሉ የሚባሉት የሐገሬዉ ወጣቶች በሕገ-ወጥ የዉጪ ሐገር ነዋሪዎች በተለይ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚፈፅሙት በደል በየሐገሩ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን ለተቃዉሞ ሠልፍ እያሳደመ ነዉ።የኢትዮጵያዉያን ትኩረት ሳዑዲ አረቢያ ላይ ባነጣጠረበት ባሁኑ ወቅት በሌሎች ሐገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተበደልን ነዉ ይሉ ይዘዋል።ስደተኞቹ እንደሚሉት የየሐገሩ ባለሥልጣናት ያስሯቸዋል፥ ያንገላቷቸዋል፥ ያስፈራሯቸዋል፥ ቀለል ሲል ደግሞ ጉቦ ይጠይቋቸዋል።በየሥፍራዉ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ለዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች በየጊዜዉ አቤት ቢሉም እስካሁን የረዳቸዉ የለም።

ኢትዮዮጵያዊዉ ወጣት ይሰደዳል።የሌሎች ስደተኞች ስቃይን እየሰማም፥ ባገኘዉ አጋጣሚ፥ በቀለለዉ አቅጣጫ በገፍ ይሰደዳል።አቅጣቸዉ ወደ አዉሮጳ ከሆነ የሳሕራ በረሐን ለማቋረጥ ሲሞክር በዉሐ-ጥም ይሰቃያል፣ የጠናበት ይሞታል።በአጋቾች ይታፈናል፥ ይደፈራል፥ ይገረፋል፥ አካሉ እየተተለተለ ይቸበቸባል።በረሐዉን ማቋረጥ የቻለዉ፥በባሕር ወሐ-መበላት ይጠብቀዋል።

One of the seventy survivors of an incident where over forty others suffocated to death in a truck container, is treated in the regional hospital in the capital Dodoma, Tanzania Wednesday, June 27, 2012. An official in Tanzania says that 43 Ethiopian and Somali nationals suffocated in the truck they were being smuggled in and Tanzania's state television said the bodies were thrown off the truck and dumped in the bush after the driver of the truck realized some of the people he was smuggling had perished. (Foto:Khalfan Said/AP/dapd)

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች አምና-ታንዛኒያእሱና ብጤዎቹ ምናልባት አዉሮጳን እያለሙ ወደ ሜድትራኒያን ባሕር አንጋጠዉ ይሆን-ይሆናል።መከራዉ ግን የሳሕራ-በረሐን እስኪረግጥ አልጠበቀዉም።ወደ ሱዳን ቀረበበት።

በየመን-አሳብሮ በነዳጅ ሐብት ከበለፀጉት የአረብ ሐገራት ለመድረስ ያለመዉ የአቀባባይ ደላሎችን ዱላ፥የአጋቾችን አፈና ካለፉ ከባሕር-ማዕበል፥ ከየመን በረሐና በረሐኞች ጋር መጋፈጥ ግዱ ነዉቁልቁል-ደቡብ አፍሪቃ ለመድረስ የሚሹ የኬንያን ጠረፍ ከረገጡበት ጊዜ ጀምሮ፥ የደላሎች፥ የወረበሎች፥ የድንበር ተቆጣጣሪዎች ዘረፋ፥ ዱላ፥ እስራትን፥ በብረት ሰንዱቅ ታፍኖ አለያም፥ሐይቅ ዉስጥ ተደፍቆ መሞትን ለመጋፈጥ መቁረጥ አለባቸዉ።እሱ ብዙዉን መከራ አልፎ፥ ሞትን አምልጦ ደቡብ አፍሪቃ ሲገባ-እፎይ የሚል መስሎት ነበር። ግን ሌላ ፍዳ-ጠበቀዉ። ሌላዉ ከደቡብ አፍሪቃ ተመሳሳይ አቤቱታ ያሰማል፤ ገና ከኬንያ ያለለፉትም-ችግር አልራቃቸዉም።

ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ


Audios and videos on the topic