የኢትዮጵያን ቡና ማስተዋወቂያ ዝግጅት በፓሪስ | ኤኮኖሚ | DW | 20.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያን ቡና ማስተዋወቂያ ዝግጅት በፓሪስ

የኢትዮጵያን ቡና ወደ አዉሮጳ በብዛት በማስገባት ጀርመን ቀዳሚነቱን ይዛ ብትገኝም ፈረንሳይ ከዓመታዊ የቡና ፍጆታዋ ስድስት በመቶዉን የምታስገባዉ ከኢትዮጵያ መሆኑ ተሰምቷል። ሰሞኑን በፓሪስ ፈረንሳይ የኢትዮጵያን ቡና ፤ የኢትዮጵያን ባህልና የጥበብ ሥራዎችን የሚያስተዋዉቅ ዝግጅት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ለአንድ ወር የሚዘልቀዉን የኢትዮጵያን ቡና የማስተዋወቁን ተግባር የሚያከናዉነዉ የዛሬ አስር ዓመት የተመሠረተዉ ካፌዎቴክ የተሰኘ ድርጅት ነዉ። የዚህ ድርጅት መስራች ቀደም ሲል የጓቲማላ አምባሳደርና የተመ የትምህርት የሳይንስና ባህል ድርጅት ቋሚ መልዕክተኛ የነበሩት ግሎሪያ ሞንቴኔግሮና ቤተሰቦቻቸዉ ናቸዉ። አነሳሳቸዉም ከተለያዩ ሃገራት የሚያስመጧቸዉን ጥራት ያላቸዉ ቡናዎች ሳይደባልቁ በየራሳቸዉ የንግድ ምልክትነት አፍልተዉ ለቡና ወዳጅ ፈረንሳዉያንና ለሌሎችም አዲስ የቡና ንግድን ለማስተዋወቅ በሚል ነበር። ሆኖም እንዳሰቡን ይህን ሥራ ሲጀምሩት ቀላል ሆኖ እንዳላገኙት ወይዘሮዋ ዛሬም ያስታዉሳሉ። የኢትዮጵያ ቡና መተዋወቅበት በጀመረበት ሳምንት በስፍራዉ የተገኘችዉ የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ አነጋግራቸዉ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች።

ሐይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic