የኢትዮጵያን ቅርስ ለመመለስ የተዘጋጁት ትውልደ ኢትዮጵያዊ | ዓለም | DW | 02.10.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የኢትዮጵያን ቅርስ ለመመለስ የተዘጋጁት ትውልደ ኢትዮጵያዊ

ኔዘርላንድ ለረዥምን ዓመታት የቆዩት እና በአሁኑ ጊዜ በአስተዳደር አማካሪነት የሚሠሩት አቶ ሲራክ አስፋው በእጃቸው ለ21 ዓመታት የኖረ የኢትዮጵያን ቅርስ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ መዘጋጀታቸውን ተናገሩ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:05

«ቅርሱ ከ20 ዓመት በላይ በግለሰብ እጅ ቆይቷል»

 ቅርሱ ወደ እሳቸው እጅ እንዴት እንደገባ ለጊዜው ለመናገር አልፈልግም ያሉት አቶ ሲራክ በ1626ዓ,ም በአጼ ፋሲለደስ ዘመነ መንግሥት የተሠራ ዘውድ በቤታቸው ከስጋት ጋር ይዘው መቆየታቸውን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። 

አቶ ሲራክ አስፋው የተባሉ እኚሁ ኢትዮ ሆላንዳዊ ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የተቀረጹበትን ይህንን ዘውድ ፣ ቤታቸው በእንግድነት የመጣ ሰው ትቶት ከሄደው ሻንጣ ውስጥ እንዳገኙት ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ተናግረዋል።

ዘውዱን እንዳዩትም የተሰረቀ መሆኑን በማሰብ፣ ኢትዮጵያ እስካልተመለሰ ድረስ ከቤታቸው እንደማይወጣ ፣ ማንነታቸውን ይፋ ላላደረጉት ዘውዱ ለተገኘበት ሻንጣ ባለቤት መናገራቸውንም ገልጸዋል። በአሁኑ ጊዜ ዘውዱ ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ ሲራክ፣ ይህን የኢትዮጵያ ታላቅ ቅርስ በቅርቡ ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እንደሚያስረክቡም ተናግረዋል። ይህ ጥንታዊ ዘውድ ከወርቅ እና መዳብ መሠራቱ ነው የተነገረው። ስለቅርሱ ዛሬ ዜናውን ያፋ ካደረጉ በኋላ ወደሚገኙበት ስልክ በመደወል አነጋግረናቸዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች