የኢትዮጵያና የደቡብ አፍሪቃ ግንኙነት፤ | ኢትዮጵያ | DW | 28.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያና የደቡብ አፍሪቃ ግንኙነት፤

የ«ብሪክስ» አገሮች የመሪዎች ጉባዔ በተደመደመ በማግሥቱ ፣ ዛሬ በዚያው በደርበን፣ የደቡብ አፍሪቃ ፣ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚንስትር Maite Nkoana-Mashabane ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድኀኖም ገ/የሱስ ጋር

3ኛውን የጋራ የሚንትሮች ሰብሰባ ከፍተዋል። በአፍሪቃው ቀንድ የምትገኘው ፣ የአፍሪቃ ኅብረት ዋና ማዕከል ኢትዮጵያና በክፍለ ዓለሙ ደቡባዊ ጫፍ የምትገኘው በኤኮኖሚ ረገድ ከአፍሪቃ ቅድሚያውን ቦታ የያዘችው ሀገር ግንኙነት እንዴት ነው የሚገመገመው?

Haile Selassie

ለሁለቱ ሀገሮች ትስስር የሚጠቀሱት አፄ ኃይለ ስላሴ

ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪቃ፤ በመልክዓ ምድር አቀማመጥ ፣ በሺዎች ኪሎሜትር የተራራቁ ናቸው፣ በጋራ ፤ በአፍሪቃ አቀፍና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች በመምከር መዝከር ረገድ እንደሚግባቡ ፤ እንዲያውም ስልታዊ ተባባሪዎች መሆናቸውን የሚናገሩት ሀገራት፣ ወዳጅነታቸውም ሆነ ተቀራራቢነታቸው እንዴት ይታያል ፣ አንድርውስ አታ አሳሞዋ እንዲህ ይላሉ።

«በአያሌ ማይሎች ቢራራቁም፤ ሁለቱም አገሮች፤ በተለያዩ ደረጃዎች፣ እጅግ ስልታዊነት ባላቸው ጉዳዮች ሠርተዋል። ይህ የስልታዊ ጉዳዮች ተባባሪነታቸውን የሚገልጸ ነው። ድቡብ አፍሪቃ ውስጥ፤ በዘር አድልዎ(አፓርታይድ)ሥርዓት ዘመን፤ ኢትዮጵያ ይኸው ዘረኛ ሥርዓት ይወገድ ዘንድ በመጀመሪያ ጉዳዩን አንሥታተንቀሣቅሳለች። ጸረ-አፓርታይድ ታጋዮች እንዲደራጁናእንዲዋጉ በማብቃቱ ረገድ አስተዋጽዖ ያደረገች ሀገርም ናት ፣ኢትዮጵያ!ለብዙዎቹም ድጋፏን ሰጥታለች። አፓርታይድን ለማስወገድ በተደረገው ርብርብ፤፤ ኢትዮጵያ ቁልፍ የሆነ ሚና በመያዝ ድርሻውን በተግባር ተወጥታለች።»

Bildergalerie Apartheid

ኔልሰን ማንዴላ ከቀድሞ ባለቤታቸዉ ጋር

የዘረኛው ሥርዓት ከተወገደ በኋላ፤ ሁለቱ ሃገራትአፍሪቃ አቀፍ ጉዳዮችን በማንቀሳቀስ ጠቃሚ ድርሻ ማበርካታቸውም ነው የሚነገርላቸው። በመካከላቸው፤ በአያሌ የትብብር ዘርፎች እንደሠሩ፤ እ ጎ አ በ 2008 ዐቢይ የጋራ የሚንስትሮች ኮሚሽን ም እንዳቋቋሙ የጠቀሱት አሳሞዋ፣ ለኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪቃ ትብብር መጠናከር ምክንያቶች ናቸው ያሏቸውን አንዳንድ ጎላ ያሉ ሁኔታዎች ከንግዱ ልውውጥ ይዞታ ጋር አያይዘው ሲያወሱ--

«በደቡብ ፤ ግዙፏ ደቢብ አፍሪቃ ፤ በአፍሪቃው ቀንድም፤ ተሰሚነት ያላት ሀገር ኢትዮጵያ ስትሆን፣ ሁለቱም ፤ ሱዳንንና ሶማልያን በመሳሰሉ አገሮች፣ ሰላም ይሠፍን ዘንድ የተቻላቸውን አድርገዋል። እናም እነዚህ ጠቃሚ ጉዳዮች ናቸው፤ ሁለቱን አገሮች ጠንክረው እንዲሠሩ የሚገፋፏቸው። እንደሚመስለኝ የጋራ ግንኙነታቸውን የሥልታዊ ጉዳዮች ተባባሪዎች ማለታቸው፤ ይበልጥ በጋራ ሥልታዊ መንገድ በመሥራታቸው ነው።

የንግዱን ግንኙነት ብንወስድ ሁለቱ አገሮች፤ እርስ-በርስ ብዙ ሊጠቃቀሙ ይችላሉ። ኢትዮጵያ 80 ሚሊዮን ገደማ ህዝብና ያልተነኻ ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት አላት። ደቡብ አፍሪቃ፤ የፋይናንስ አቅምና የሥነ ቴክኒክ ዕውቀት አላት። እናም ያን ሀብት ሥራ ላይ የማዋል ችሎታ አላት። ከተለያየ አቅጣጫ ሲመለከቱት ሁለቱ አገሮችበተለያዩ ዘርፎች መተባበራቸውን መገንዘብ ይችላል። ግንኙነታቸው ይበልዝ በሥልታዊ አያያዝ ላይ ያተኮረ ነው እየተባለ የሚጠቀሰውም ለዚህ ነው።»

የንግድ ግንኙነትን አሁን በጨረፍታ አውስተዋል። የቅርብ ጊዜው ሠንጠረዥ እንደሚያሳየው ከሆነ፣ 302 ሚሊዮን ራንድ(32,82 ሚሊዮን ዶላር)የሚያወጣ የንግድ ልውውጥ ነው በሁለቱ አገሮች መካከል የተደረገው። በአፍሪቃ ደረጃ ይህ መጠን የቱን ያህል ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ ነው? ለአንድርውስ አታ አሳሞዋ ያቀረብኩላቸው ሌላው ጥያቄ ነበር።

«አፍሪቃ ውስጥ በአፍሪቃውያን መካከል የንግዱ ልውውጥ በጣም አነስተኛ ነው። ብዙውን ጊዜ እንደምናየው፤ እንደምንሰማው፤ በቁጥር ላቅ ያሉ የአፍሪቃ አገሮች፤ የሚገበያዩት ከአውሮፓ ወይም ከአንዳንድ የዓለም ክፍሎች ጋር ነው። በአፍሪቃውያን መካከል፤ የሚደረገው የእርስ-በርስ የንግድ ልውውጥ ግን በጣም ዝቅ ብሎ ነው የተገኘው።»

ትናንት ፣ የ«ብሪክስ» አገሮች የመሪዎች ጉባዔ ተጠናቋል። በዚህ ጉድኝት ከአፍሪቃ የተወከለች ብቸኛ ሀገር ደቡብ አፍሪቃ ብቻ ናት። ይህ ለመላው ክፍለ-ዓለም የሚሰጠው ጠቀሜት ምንድን ነው?

«እንደሚመስለኝ ፣ በይበልጥ ምልክት ነው። ለክፍለ ዓለሙ!በአሁኑ ጊዜ የአፍሪቃ አገሮች ምን ማድረግ እንደሚችሉ የሚጠቁም ምልክት (ዓርማ) ነው መስሎ የሚታየው። በዛ ያሉ ፣ ናይጀሪያን የመሳሰሉ አገሮች፣ ሌሎችም ደረጃቸው፤ ከ«ብሪክስ» አገሮች ድርጅት እንዲመደብ በጉጉት ይጠባበቃሉ።

በብሪክስ አገሮች መካከል የንግድ ግንኙነት ከተጠናከረ፣ የአካባቢው ኃይል መንግሥት ደቡብ አፍሪቃ ከምታገኘው ትርፍ አኳያ ሳይሆን ፣ ክፍለ ዓለሙ እንቅሥቃሴውን በትጋት ያጠናክራል፤ ተስፋ የምናደርገው በተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች መነቃቃትን እንደሚፈጥር ነው።

ይህ በአጠቃላይ ለደቡብ አፍሪዋቃ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪቃ በመላ ጠቃሚ ግሥጋሤን የሚያስከትል ይሆናል።»

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ