1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የእስራኤል ዘመን መለወጫ በጋራ ተከበረ

ሐሙስ፣ መስከረም 10 2016

«ሻናቶቫ ማለት በዕብራይስጥ መልካም በዓል ማለት ነዉ። ግን ለአንድ እስራኤላዊ መልካም በዓል ሲባል፤ ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ ባሉት አስር ቀናት የንሰሃ ሳምንት በመሆኑ ሻናቶቫ መልካም በዓል የተባለዉ እስራኤላዊ ሻናቲቩ ይላል። ይህ ማለት በአዲሱ ዓመት በህይወት መዝገብ ተመዝገብ እንደማለት ነዉ።» የፅዮናዊነት አራማጅ አቶ መስፍን አሰፋ

https://p.dw.com/p/4WcTI
የእስራኤላዉያን  5784 አዲስ ዓመት
የእስራኤላዉያን  5784 አዲስ ዓመትምስል Ethio Beteisrael

የቤተ-እስራኤላውያን የአዲስ ዓመት አከባበር በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩት ቤተ እስራኤሎች በየምኩራቦቻቸው በመገኘት ቀንደ መለከት (ሼፋር) በመንፋት አክብረውታል


«ሻናቶቫ ማለት በዕብራይስጥ መልካም በዓል ማለት ነዉ። ግን ለአንድ እስራኤላዊ መልካም በዓል ሲባል፤ ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ ባሉት አስር ቀናት የንሰሃ ሳምንት በመሆኑ ሻናቶቫ መልካም በዓል የተባለዉ እስራኤላዊ ሻናቲቩ ይላል። ይህ ማለት በአዲሱ ዓመት በህይወት መዝገብ ተመዝገብ እንደማለት ነዉ።»  የኢትዮጵያ ቤተ-እስራኤላዉያን የፅዮናዊነት አራማጅ እና የአፍሪቃ አይሁዳዉያን የምርምር እና ጥናት ማዕከል አባል አቶ መስፍን አሰፋ ነበሩ።

መስፍን አሰፋ: የኢትዮጵያ ቤተ-እስራኤላዉያን የፅዮናዊነት አራማጅ እና የአፍሪቃ አይሁዳዉያን የምርምር እና ጥናት ማዕከል አባል
መስፍን አሰፋ: የኢትዮጵያ ቤተ-እስራኤላዉያን የፅዮናዊነት አራማጅምስል Mesfin Assefa

የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤያዉያንን ጨምሮ በዓለም ዙርያ የሚገኙ እስራኤላዉያን ባለፈዉ አርብ ምሽት አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫን ሲቀበሉ  በእብራይስጥ ቋንቋ የተለዋወጡት የአዲስ ዘመን የመልካም ምኞት መግለጫ ነዉ። የኢትዮጵያ አዲሱ 2016 ዓመት በገባ በአራተኛዉ ቀን አርብ ምሽት ላይ አዲሱ የአይሁዳዉያን ዓመት መከበርጀምሮ ቅዳሜ መስከረም አምስት እለት የእስራኤላዉያን  5784 አዲስ ዓመት አንድ ብሎ ጀምሯል። እስከ ባለፈዉ እሁድ ድረስም የዘመን መለወጫ በእስራኤላዉያን ዘንድ በድምቀት ተከብሯል። የእስራኤል መንግሥት ምስረታ 75ኛ ዓመት
ኢትዮጵያዉያን እና አይሁዳዉያን የዘመን መለወጫን የሚያከብሩት መስከረም ወር ላይ ነዉ፤ በመሃል ጳጉሜ ወር በመኖሩ ቀኑ ይለያያል እንጂ ሁለቱ ሃገራት የዘመን መለወጫን አንድ ላይ ነዉ የሚያከብሩት ያሉን በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት የኢትዮጵያ ቤተ-እስራኤላዉያን የፅዮናዊነት አራማጅ እና የአፍሪቃ አይሁዳዉያን የምርምር ጥናት ማዕከል አባል አቶ መስፍን አሰፋ፤ ዘንድሮ በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የእስራኤል ኤምባሲ በኢትዮጵያ የእስልም እና የክርስትና እምነት ተከታዮችን ታዋቂ ሰዎችን እንዲሁም ወደ እስራኤል ለመሄድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ቤተ እስራኤላዉያንን ጋብዞ  የኢትዮጵያ እና እስራኤላዉያን አዲስ ዓመት በአንባሳደሩ መኖርያ ቤት ቅጽር ግቢ በድምቀት መከበሩን ነግረዉናል። 
«የኢትዮጵያ እና የእስራኤል አዲስ አመት ወይም የዘመን መለወጫ ብዙ ጊዜ መስከረም ወር ላይ ይገናኛሉ። አንዳንድ ጊዜ በሳምንት ብሎም አንዳንድ ጊዜ በጥቂት ቀናት ይራራቃሉ። ዘንድሩ የእስራኤል አዲስ ዓመት የዋለዉ፤  
ኢትዮጵያ ዉስጥ የሀገሪቱ እና የእስራኤል የዘመን መለወጫዎች የሁለቱ ሃገር ዜጎች በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች መገኘታቸዉን አቶ አሰፋ ተናግረዋል። ሀኑካ አዲስ አበባ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ በአደባባይ ላይ ተከበረ
የቤተ-እስራኤላውያን የአዲስ አመት አከባበር በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩት ቤተ እስራኤሎች በየምኩራቦቻቸው በመገኘት ቀንደ መለከት (ሼፋር) በመንፋት አክብረውታል፡፡ የሰሜን ሸዋ ቤተ እስራኤላውያን በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው የቤተእስራኤላውያን ማእከል የ5784ኛ ውን የአይሁዳውያን አዲስ ዓመት በደመቀ ሁኔታ ማክበራቸዉን አቶ መስፍን ተናግረዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስትያን  ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ጽ/ ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር  አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ባለፈዉ ሰሞን በእስራኤል አምባሳደር ቤት በተከበረዉ የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ዘመን መለወጫ ዝግጅት ላይ ንግግር አድርገዋል።እስራኤል ከ200 በላይ የሚሆኑ ዜጎቿን ከአማራ ክልል አወጣች
የኢትዮጵያዉያንን እና የእስራኤልን የዘመን መለወጫዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሃይማኖት አባቶችን እና ሌሎች ኢትዮጵያዉያን እና እስራኤላዉያን እንግዶችን አዲስ አበባ በሚገኘዉ የመኖርያ ቅጽር ጊቢ ዉስጥ በድምቀት ያከበሩት  በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ የእስራኤል እና የኢትዮጵያን ጥንታዊ ግንኙነት እና ትስስርን በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።  
በአማራ ክልል የሚታየዉን ጦርነት ተከትሎ እስራኤል ከጎንደር ያስወጣቻቸዉ በመቶ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዉያን መካከል ጥቂቶቹ አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በጠሩት ዝግጅት ላይ ተገኝተዉ እንደነበር የኢትዮጵያ ቤተ-እስራኤላዉያን የፅዮናዊነት አራማጅ አቶ መስፍን አሰፋ ነግረዉናል። በዚህ ዝግጅት ላይ ስለ ጦርነቱ አሁንም ከጎንደር ስለወጡት ቤተ እስራኤላዉያን ተወርቶ ይሆን? 
በእስራኤላዉያን ዘንድ የሚከበረዉ አዲስ ዓመት ወይም ሰረቀ ብርሃን በይብራይስጥ ሮሻሸና ፤ ይህ በዋለ በአስረኛዉ ቀን የሚከበረዉ ዮኩፑር ወይም የንሰሃ፤ የይቅርታ በዓል፤ በግዕዙ አስተሰርዮ፤  ብሎም መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ስለሚከበረዉ «ሱኮት» ወይም ዳስ በዓል አቶ መስፍን አሰፋን በስፋት ነግረዉናል። 
ሙሉ ዝግጅቱን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ! 

የኢትዮጵያዉያንን እና የእስራኤልን የዘመን መለወጫዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሃይማኖት አባቶችን እና ሌሎች ኢትዮጵያዉያን እና እስራኤላዉያን እንግዶችን አዲስ አበባ በሚገኘዉ የመኖርያ ቅጽር ጊቢ ዉስጥ በድምቀት ያከበሩት  በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ
አለልኝ አድማሱ ኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደርምስል Mesfin Assefa
የሰሜን ሸዋ ቤተ እስራኤላውያን በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው የቤተእስራኤላውያን ማእከል የ5784ኛ ውን የአይሁዳውያን አዲስ ዓመት በደመቀ ሁኔታ አከበሩ
የሰሜን ሸዋ ቤተ እስራኤላውያን በ 5784ኛ ው የአይሁዳውያን አዲስ ዓመትምስል Ethio Beteisrael
በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የእስራኤል ኤምባሲ አዲሱን ዓመት በኢትዮጵያ የእስልም እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ጋራ ተከበረ
በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የእስራኤል ኤምባሲ አዲሱን ዓመት በኢትዮጵያ የእስልም እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ጋራ ተከበረምስል Mesfin Assefa

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ