የኢራን የአቶም ዉዝግብ | ዓለም | DW | 22.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኢራን የአቶም ዉዝግብ

ዓለም አቀፉ የአቶም ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት በምህፃሩ የአይ ኤ ኢ ኤ እና ኢራን በአጨቃጫቂዉ የአቶም መረሃ ግብር ጉዳይ አንድ ዉል ላይ ደረሰ።

ዓለም አቀፉ የአቶም ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት በምህፃሩ የአይ ኤ ኢ ኤ እና ኢራን በአጨቃጫቂዉ የአቶም መረሃ ግብር ጉዳይ አንድ ዉል ላይ ተስማማ። ይህ ዉል በቅርቡ እንደሚፈርም ዓለም አቀፉ የአቶም ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት መሪ ዩኪያ አማኖ ዛሪ ቴህራንን ጎብኝተዉ ለመመለስ በዝግጅት ላይ ሳሉ ገልጸዋል። ያም ሆኖ ስምምነት ያልተደረሱ ጥቂት ነጥቦችን ግልጽ ማድረግ እንደሚጠበቅም ሳይጠቁሙ አላለፉም ። የአይ ኤ ኢ ኤ መሪ ዩኪያ አማኖ ስለ አከራካሪው የኢራን አቶም መርሀ-ግብር ከኢራን ዋና ተደራዳሪ ሰይድ ጃሊል ጋር ለመምከር ቴህራን የገቡት ትናንት መሆኑ ይታወሳል። ኢራን ነገ ረቡዕ በኢራቅ መዲና ባግዳድ በሚካሄድ ስብሰባ ላይ የአቶም መርሃ ግብርዋን ለሰላማዊ ዘዴ ብቻ እንደምትጠቀምበት የኑክልየር ጦር መሣሪያ ለማምረት እየሞከረች ነው በሚል ወቀሳ የሰነዘረውን ምዕራቡን ዓለም ማሳመን ይጠበቅባታል።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

 • ቀን 22.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/150GN
 • ቀን 22.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/150GN