የኢራን እና ስድስቱ ታላላቅ መንግስታት ምክክር | ዓለም | DW | 02.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኢራን እና ስድስቱ ታላላቅ መንግስታት ምክክር

ጀርመንን ጨምሮ አምስቱ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ቋሚ አባላት አሜሪካ ሩስያ ቻይና እንግሊዝ እንዲሁም ፈረንሳይ፣ በኢራን የኒኩልየር ግንባታ ዙርያ ለመጀመርያ ግዜ በስዊዘርላንድ ጄኔቭ ላይ መምከር የጀመሩ ሲሆን

default

በስዊዘርላንድ ጄኔቭ በመምከር ላይ

ዉይይቱ በመግባባት መከናወኑ እና በመቀጠል በቅርቡ እንደገና ዉይይት ለማድረግ መስማማታቸዉ ተዘግቦአል። ከዚሁ ጎን ለጎን ላላፉት 30 አመታት በባላጣነት ይተያዩ የነበሩት የአሜሪካ እና የኢራን መንግስታት ተደረዳሪዎች፣ የተናጠል ዉይይት ማድረጋቸዉ ተጠቁሞአል። ይህም ሆኖ ከኢራን ስለሚጠበቀዉ የኑክልየር ጣብያን ማስፈተሽም ሆነ፣ በቅርቡ ይፋ የሆነዉ የኑክልየር ጣብያ የዉይይቱ ዋንኛ የመነጋገርያ አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ቢገመትም፣ በዚህ ረገድ ተደራዳሪዎች ስለደረሱበት ስምምነት ይፋ የወጣ መግለጫ አለመኖሩ ተነግሮአል። ዝርዝሩን የሳዉዲአርብያዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ልኮልናል።

ነብዩ ሲራክ ፣ አዜብ ታደሰ፣ አርያም ተክሌ