የኢራቅ ጦርነት አራተኛ ዓመት | ዓለም | DW | 19.03.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኢራቅ ጦርነት አራተኛ ዓመት

ማዕከላዊ ባግዳድ ውስጥ የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስና አጋሮቿ የኢራቅን ጦርነት ከጀመሩ ዛሬ ልክ አራት ዓመት ሞላው ። የዘመቻው ዓላምም የሳዳም ሁሴንን መንግስት መጣልና ኢራቅ አሏት ተብሎ ከተገመተው ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪዎች ዓለምን መታደግ ነበር ። ይሁንና ዛሬ ከአራት ዓመት በኃላ የኢራቅ ጦርነት አላበቃም ። አንድ መቶ አርባ ሺህ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ኢራቅ ይገኛሉ ። ያኔ አለ ተብሎ በስፋት የተነገረለት ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳ

default

�ያ አልተገኘም ።

የኢራቁ ጦርነት ሲጀመር ከዩናይትድ ስቴትስ በኩል ከመነሻው ጦርነቱን በድል የመወጣቱ ተስፋ ነበር ።ጦርነቱ በተጀመረ በስድስተኛው ሳምንት ላይ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ አብርሀም ሊንከን ከተባለው የዩናይትድ ስቴትስ የጦር መርከብ ላይ ለወታደሮቻቸው ባሰሙት ንግግር ዓላማችን ግቡን መቷል ዓይነት መልዕክት ነበር ያስተላለፉት ።
ድምፅ
“በኢራቅ ዋነኛዎቹ የውጊያ ዘመቻዎች ተጠናቀዋል ። በኢራቁ ውጊያ ዩናይትድ ስቴትስና አጋሮቻችን የበላይነቱን ይዘዋል ።”
ከአራት ዓመት በኃላ ግን ጆርጅ ቡሽ የተናገሩት ከያኔው የድል ዜናቸው ጋር ፈፅሞ አይገናኝም
“የኢራቅን ሁኔታ የአሜሪካ ህዝብ አይቀበለውም ። ለኔም እንደዚሁ ተቀባይነት የለውም ።”
ባለፉት አራት ዓመታት በተካሄደው የኢራቁ ጦርነት ቁጥራቸው ከሶስት ሺህ ሁለት መቶ በላይ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ተገድለዋል ። በይፋ የሚነገረው የቁስለኞቹ ቁጥር ደግሞ ከሀያ አራት ሺህ በላይ ነው ። የየዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታጎን በቅርቡ ባወጣው ዘገባ ከአራቱ ዓመት የጦርነት ጊዜ ውስጥ እ.አ.አ የሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ ምህረት የመጨረሻዎቹ ሶስት ወራት በርካታ ጥቃቶች የተፈፀሙባቸውና እጅግ በርካታ ሰዎች የተገደሉባቸው ወራት በመሆን ተመዝግበዋል ። የተወሳሰበው አካሄድ ሲታይ እንዲያውም በሀገሪቱ የርስ በርስ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ በዚህ ወቅት ነው ለመጀመሪያ ጊዜ መነገር የጀመረው ። ይሁንና ቡሽ በአዲሱ ዕቅዳቸው ለኢራቁ ጦርነት የሚያስፈልገው ተጨማሪ ወታደር ቁጥር ወደ ሀያ አንድ ሺህ አምስት ወታደሮች እንደሚያስፈልጉ ነው ያሳወቁት ። በዚሁ መሰረት ተጨማሪ አራት ሺህ ሰባት መቶ ወታደሮች በቅርቡ ወደ ባግዳድ ይላካሉ ። የእስካሁኑ የጦርነት ስልት ካላዋጣ ተጨማሪ ወታደሮች ወደ ኢራቅ መላኩ ምን ለውጥ ያመጣል የሚለው የኢራቅ ጦርነት ተችዎች ደጋግመው የሚያነሱት ነጥብ ነው ። ዲሞክራቶችም የአሜሪካን ወታደሮች ከኢራቅ የሚወጡበት ጊዜ እንዲቆረጥ የበኩላቸውን ሙከራ አድርገዋል ። አሜሬካን ህግ መሰሰኛ ምክርቤት ውስጥ የሚገኙት ዲሞክራቶች ወታደሮቹ ከኢራቅ የሚወጡበት ቀን እንዲቆረጥ ውሳኔ ለማሳለፍ ያደረጉት ሙከራ ግን አልተሳካም ። አሜሪካን መውጫ ባጣችለት የኢራቅ ጦርነት ሪፐብሊካኖችም ሆነ ዲሞክራቶች ደስተኛ አይደሉም ። የአሜሪካን ወታደሮች ኢራቅ መቆየት የሚፈይደው ጉዳይ ለብዙዎቹም ግልፅ አይደለም ። የብዙዎቹ ጥያቄ ከዲሞክራቱ ጆ ቢደን ጥያቄ ጋር ይመሰላል ።
“ለምንድን ነው ወታደሮቻችን ኢራቅ እንዲቆዩ የምንፈልገው ? የርስ በርስ ጦርነት ለመዋጋት ነው ? ወይስ ጥቅማችን ለማስከበር የሚረዱ ሁኔታዎችን ብቻ ለማመቻቸት ? አልቃይዳ ግዛቱን እንዳይዝ ለመከላከል ? የኢራቅ ኃይሎችን ማሰልጠን እና ወታደሮቻችንን መጠበቅ ? ይህን ለማድረግ እጅግ በጣም አነስተኛ ወታደር ነው የሚያስፈልገን ። “
ይህ ጥያቄ እስካሁን ተገቢውን መልስ አላገኘም ። ከሪፐብሊካኖች አንዳንዶቹ ደግሞ ከተጨባጩ ሁኔታ ጋር የማይሄደውን የአሜሪካን ወታደሮች ከኢራቅ ይውጡ የሚለውን ሀሳብ መከላከላቸውን እንደሚገፉበት ነው ያሳወቁት ። ከነዚህ አንዱ የሪፐብሊካኑ ሚች ማክኮኔል ናቸው ።
“ሪፐብሊካኖች ፣ ለአጋሮቻችንና ለወታደሮቻችን መልዕክት አላቸው ። መልዕክቱም ይህ ነው ። ከድርጊቶችና ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ግንኙነት የሌለውን ከኢራቅ እንውጣ የሚባልበት የጊዜ ሰሌዳን ጉዳይ መከላከላችንን እንቀጥላለን ። የጀነራል ፖትርያስ ተልዕኮ እንዲሳካ ዕድል እንሰጣለን ። ጀነራሉ ባከናወኑት ተግባር እንኮራለን ። ስራው እስኪፈፀም ድረስ ከጎናቸው እንቆማለን ። “
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ አሁንም ከኢራቅ መውጣት ማለት ለጠላት እጅ መስጠት ማለት ነው በሚለው አቋማቸው እንደፀኑ ነው ። ሆኖም ግን በቅርቡ በተሰበሰበ መጠይቅ መሰረት ከአሜሪካን ህዝብ ስልሳ በመቶው የአሜሪካን ወታደሮች በመጪው አንድ ዓመት ውስጥ ከኢራቅ ይውጡ ባይ ነው ።