የኢሕአዴግ ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞ-ዉይይት | ኢትዮጵያ | DW | 06.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢሕአዴግ ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞ-ዉይይት

የግንባሩን መሪዎች መርጧልም።እስካሁን ባለዉ ልምድ መሠረት የግንባሩ ዉሳኔዎችና መሪዎች ማለት የኢትዮጵያ ፖሊሲ ወይም መርሕና መሪዎች ናቸዉ። ጉባኤዉንና ዉሳኔዎቹን ለዚሕ ሳምንት ዉይይታችን ርዕስ ያደረግነዉም ዉሳኔ፤ ምርጫዉ መላዉ ኢትዮጵያን ሥለ ሚነካ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 26:28
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
26:28 ደቂቃ

የኢሕአዴግ ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞ-ዉይይት

ኢትዮጵያን ለ24 ዓመታት የመራዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) 10ኛ መደበኛ ጉባኤዉን ባለፈዉ ሰኞ አጠናቅቋል።ከነሐሴ 22 እስከ 25 መቀሌ-ትግራይ ዉስጥ የተደረገዉ ጉባኤ ከመጠናቀቁ በፊት በተለያዩ ድርጃታዊና ሐገራዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋግሮ ዉሳኔዎችን አሳልፏል።የግንባሩን መሪዎች መርጧልም።እስካሁን ባለዉ ልምድ መሠረት የግንባሩ ዉሳኔዎችና መሪዎች ማለት የኢትዮጵያ ፖሊሲ ወይም መርሕና መሪዎች ናቸዉ። ጉባኤዉንና ዉሳኔዎቹን ለዚሕ ሳምንት ርዕስ ያደረግነዉም ዉሳኔ፤ ምርጫዉ መላዉ ኢትዮጵያን ሥለ ሚነካ ነዉ።

እንደተከታተልነዉ ዉይይት የተደረገባቸዉ ርዕሶች፤ የተላለፉት ዉሳኔዎች፤ ለግንባሩ መሪነት የተመረጡት ባለሥልጣናትም ብዙ በመሆናቸዉ በዚሕ አጭር ጊዜ ልንዘረዝራቸዉ አንችልም።በጉባኤዉ ከተነሱት የጎሎ በመሠሉን ሰዎስት ጉዳዮች ላይ ለማተኮር እንሞክራለን።ልማት፤የመልካም አስተዳደር እጦት፤ እና መተካካት።

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic