የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ጉባኤ | ኢትዮጵያ | DW | 26.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ጉባኤ

(ደሕዴግ) ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝን የፓርቲዉ ሊቀመንበር አድርጎ በድጋሚ መርጧቸዋል።የግንባሩን መሥራች ዶክተር ካሱ ኢላላን ደግሞ አሰንብቷል።የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በበኩሉ የቀድሞዉን የፓርቲዉን ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ለገሠን ጨምሮ ቢያንስ ሠወስት ነባር ባለሥልጣናቱን አሰናብቷል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:09
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:09 ደቂቃ

የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ጉባኤ

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የኢሕአዴግ ተጣማሪ ፓርቲዎች በየአካባቢያቸዉ የየራሳቸዉን ጉባኤ እያደረጉ ነዉ።ከአራቱ ፓርቲዎች ቀደም ብሎ ጉባኤዉን ያገባደደዉ የደቡብ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ደሕዴግ) ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝን የፓርቲዉ ሊቀመንበር አድርጎ በድጋሚ መርጧቸዋል።የግንባሩን መሥራች ዶክተር ካሱ ኢላላን ደግሞ አሰንብቷል።የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በበኩሉ የቀድሞዉን የፓርቲዉን ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ለገሠን ጨምሮ ቢያንስ ሠወስት ነባር ባለሥልጣናቱን አሰናብቷል።የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) እና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) ጉባኤዎች ነገ ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

 

Audios and videos on the topic