የኢሕአዴግ ምክር ቤት መግለጫና አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 17.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢሕአዴግ ምክር ቤት መግለጫና አስተያየት

ገዢው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢሕአዴግ ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ አጠናቀቀ። መግለጫውን እንዳነበቡት ለዶይቼ ቬለ DW የገለፁት አንድ የፖለቲካ ምሁር በርካታ አሳሳቢ ጉዳዮች እያሉ ያንን ያላነሳ እና የተድበሰበሰ ነው ብለውታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:46

«መግለጫው ግልፅነት ይጎድለዋል፤ ብዙ ጉዳይ እያለ ተድበስብሷል»

 የግንባሩ ምክር ቤት ጉባኤውን አጠናቅቆ ባወጣው መግለጫ ባለፈው ስብሰባው ያሳለፋቸውን ዋና ዋና ያላቸውን ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች መሠረት በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ተጨባጭ ርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውን በዚህ ስብሰባው  በዝርዝር መመልከቱን ጠቅሷል። ከዚህም ሌላ ምክር ቤቱ በእህት ድርጅቶችና በአመራሩ መካከል የሚታየውን መጠራጠር በመፍታት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከሩንም አመልክቷል። የምክር ቤቱ መግለጫ አክሎም የኤኮኖሚ ይዞታውን፤ እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን አዘጋገብን የሚመለከቱ ጥቅል ሃሳቦችንም አንስቷል። በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል መኮንን መግለጫው ወትሮም የሚታወቀው ኢህአዴግ አለመለወጡን ያሳያል ይላሉ። መግለጫውን መነሻ በማድረግ አስተያየታቸውን ጠይቄያለሁ።  

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic