የኢሕአዴግና የተቃዋሚዎቹ ድርድር | ኢትዮጵያ | DW | 13.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢሕአዴግና የተቃዋሚዎቹ ድርድር

የኢሕአዴግ እና የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) ድርድር፤ የኢሕአዴግና የኦጋዴን ነፃ አዉጪ ግንባር ድርድር፤ የኢሕአዴግና የቅንጅት ድርድር፤ የኢሕአዲግና የተቃዋሚዎች ዉይይት ወይም ስምምነት ሌሎችም ዛሬ አንድም ተረስተዋል-አለያም የነበር ዝክር ናቸዉ።አበሻ ተስፋ አይቆርጥ ይሆናል።የዚያኑ ያክል «ቀን እባብ ያየ ማታ በልጥ በረየ» ይላልም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 13:46

የኢሐዴግና የተቃዋሚዎቹ ድርድር

በራቀዉ ዘመን ከናይጄሪያ እስከ ሱዳን፤ ከዚምባቡዌ እስከ ቻድ የሚገኙ ፖለቲከኞች ይደራደሩ፤ ይወያዩ ይታረቁባት ነበር።በቅርቡ ሶማሌዎች ተደራድረዉባታል።ደቡብ ሱዳኖች ይደራደሩ-ይስማሙባታል። ድፍን አፍሪቃ ይመክር-ይዘክርባታል።ኢትዮጵያ።ኢትዮጵያዉያንን ግን ማጣላት፤ ማዋጋት፤ ማገደል ማሰደዷ እንጂ ማስማማትዋ አይታወቅም።ሰኔ 1983 የጦርነት፤መጠፋፋቱ ፖለቲካ «አበቃ» ያሉን ፖለቲከኞቿ እንደ ወዳጅ ባንድ አዳራሽ መክረዉ እንደጠላት ለመገዳደል ዓመት አልፈጀባቸዉም።እስካሁንም ድርድር ዉይይት በተባለ ማግሥት መካካድ፤ መጣላት፤ መጋጨት የኢትዮጵያዉያን ፖለቲከኞች «መለያ» መስሏል።ደግሞ ሰሞኑን ድርድር ዉይይት እያሉ ነዉ።ካለፈዉ ይለይ ይሆን? የዛሬ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ። ላፍታ አብረን እንጠይቅ። 
                       
በልማዱ የሰኔ ሐያ-አራቱ ጉባኤ ብለን የምንጠራዉ ስብሰባ ከተደረገ 26ኛ ዓመቱን ሊደፍን ወራት ቀሩት።ያኔ የሽግግር መንግሥቱን ከመሠረቱት የፖለቲካ ፓርቲዎች አብዛኞቹ ከስመዋል።ሌሎቹ በሌላ ተተክተዋል ወይም በሥም ብቻ ቀርተዋል። የተቀሩት ተሰደዋል።ያኔ ከሒልተን ሆቴል የተንቆረቆረዉ  የመናገር፤ የመፃፍ፤ በነፃ የመደራጀት መብት፤ የፍትሕ ተስፋም ዛሬ አለ ማለት በርግጥ ያሳስታል።ጉባኤዉን የጠራ፤ያስተናገደና የመራዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር  (ኢሕዴግ) ግን ከያኔዉ ብዙ ጠንክሮ እንደነበረ ሥልጣን ላይ  አለ።በ25 ዓመት ከመንፈቁ ፖለቲካዊ ጉዞ የነበሩና ያሉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች  ከገዢዉ ፓርቲ ጋር ለመደራደር በየጊዜዉ ጠይቀዋል።በተለይ በምርጫ ዋዜማና ማግሥት ብዙ ድርድር ዉይይቶች፤ ጥቂት ስምምነቶች ተደርገዋልም። ድርድር ዉይይት ስምምነቶቹ ሁሉ ግን በገዢዉ ፓርቲ እንጂ በተቃዋሚዎች ጥያቄ የተደረጉ አልነበሩም።አንድም ድርድር ና ዉይይት ለዘላቂ ዉጤት አልበቃምም።

ዘንድሮም ድርድር፤ ዉይይት አለ።«ጥሩ ነዉ» ይላሉ የቀድሞዉ የምክር ቤት እንደራሴ እና የቀድሞዉ

Karte Äthiopien englisch

የአንድት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ።የፖለቲካ ተንታኝ እና ደራሲ ዩሱፍ ያሲን እንደሚሉት ደግሞ መነጋገር መልካም ነዉ።አበሻ ተስፋ አይቆርጥም።አቶ ግርማ እንደሚሉት ተስፋ ከመጣት ሥለሚሻል።የዘንድሮዉም ድርድር፤ ወይይት ወይም ንግግር ጋባዥ እንደከዚሕ ቀደሞቹ ሁሉ ገዢዉ ፓርቲ ነዉ።ኢሕአዴግ።በድርድሩ የሚካፈለዉ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝደንት ዶክተር ጫኔ ከበደ በገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ይሉታል።
                                 

የኢሕአዴግ እና የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) ድርድር፤ የኢሕአዴግና የኦጋዴን ነፃ አዉጪ ግንባር ድርድር፤ የኢሕአዴግና የቅንጅት ድርድር፤ የኢሕአዴግና የሕብረት ድርድር፤ የኢሕአዲግና የተቃዋሚዎች የምርጫ ማስፈፀሚያ ዉይይት ወይም ስምምነት ሌሎችም ዛሬ አንድም ተረስተዋል-አለያም የነበር ዝክር ናቸዉ።
አበሻ ተስፋ አይቆርጥ ይሆናል።የዚያኑ ያክል «ቀን እባብ ያየ ማታ በልጥ በረየ» ይላልም።ያለፈዉ ልምድ በዛሬዉ ድርድር ተስፋ ላለማድረጉ ምክንያት ወይም መሰረቱ ነዉ።እንደገና አቶ ዩሱፍ ያሲን።
                              
በዉይይት ድርድር ሒደት «መተማመንን ለመገንባት» አለያም «ጥርጣሬን ለማቃለል» የሚባሉ ተደራዳሪዎች ሊወስዷቸዉ የሚገቡ አያሌ እምጃዎች አሉ።እስካሁን ዉይይት ድርድሩ እንደሚደረግ ከመነገሩ በስተቀር ጥርጣሬን ለማቃልል የሚረዱ እርምጃዎች ሥለመወሰዳቸዉ፤ ለመዉሰድ ሥለ መታሰቡም ሆነ ሥለ መጠየቁ የተሰማ የለመ።
የተደራዳሪ ፓርቲዎች ተወካዮች፤ የአደራዳሪዉ ማንነት፤የመደራደሪያዉ ርዕስ እንዴትነት፤ የመደራደሪያዉ ሥፍራ የትነትም አንድም ሚስጥር ነዉ አለያም ገና በድርድር የሚወሰን ነዉ።የሚታወቀዉ ከነገ-በስቲያ ሮብ ድርድሩ መቀጠሉ ነዉ።21 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዢዉ ፓርቲ ጋር ለመደራደር መዘጋጀታቸዉ ነዉ።
                              
ይላሉ የኢዴፓ ፕሬዝደንት ዶክተር ጫኔ ከበደ።የተቀሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎችም እሁለት  ተቧድነዉ የየራሳቸዉን ረቂቅ ሐሳብ ማቅረባቸዉ ተዘግቧል።ገዢዉ ፓርቲም እንዲሁ።ኢሕአዴግ ከተቃዋሚዎቹ ጋር ለመነጋገር ጥሪ ያደረገዉ ሥርዓቱ በሕዝባዊ ተቃዉሞ መነቃነቅ ሥለጀመረበት ነዉ ባዮች አሉ።
ድርድሩ ዉጪ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ባለማካተቱ የገዢዉን ፓርቲ ሥልጣን ከማራዘም ባለፍ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ችግሮች ለማቃለል የሚተክረዉ የለም በማለት ይነቅፉታልም።የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፤ ጋዜጠኞች እና የመብት ተሟጋቾች ታስረዉ፤ የሐገሪቱ ሕዝብ በአስቸኳይ አዋጅ ሕግ መብቱ ተገድቦ የሚደረግ ድርድር የሚፈለገዉን ዉጤት ማምጣቱን የሚጠራጠሩም አሉ።አቶ እንደሚሉት ግርማ መፍትሔዉ ኢሕአዴግ እጅ ነዉ ባይ ናቸዉ።
                                    
የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት

ለአፍሪቃዉያን ጠቀመም-አልጠቀመ ድርጅቱ እንዲመሠረት ትልቁን አስተዋፅኦ ያደረገችዉ ኢትዮጵያ መሆንዋ አያጠያይቅም።ከአፍሪቃ ሐገራት ሁሉ ቀድማ ሁለት የተገመሰችዉም ሐገር አፍሪቃዉያንን አንድ ለማድረግ ያለመዉን ድርጅት በግንባር ቀደምትነት የመሠረተችዉ ሐገር ናት።ኢትዮጵያ።ናጄሪያዎች ቢያፍራ በተባለዉ ግዛት ሰበብ እንደ ጎርጎርያኑ አቆጣጠር በ1967 ከርስበርስ ጦርነት ሲዘፈቁ ከቀዳሚዎቹ አስታራቂዎች አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች። ሱዳኖችን ሰሜን-ደቡብ ከፍሎ ከ1955 ጀምሮ ሲያፋጅ የነበረዉ ጦርነት በ1972 የቆመዉ በኢትዮጵያ ሸምጋይነት ነበር።ከጀቡቲ እስከ ሮዴሽያ፤ከናሚቢያ እስከ ደቡብ አፍሪቃ ለነፃነት የበቁት በኢትዮጵያ ድጋፍና ርዳታ ነዉ።
የሶማሌዎች ዋና አደራዳሪ፤ የሰላማቸዉ ግንባር ቀደም አስከባሪ፤ የደቡብ ሱዳኖች አስታራቂ ኢትዮጵያ ናት።ኢትዮጵያዉያን አንድም ጊዜ ከዘላቂ ስምንነት አለመድረሳቸዉ እንጂ ዚቁ።ያሁን ተደራዳሪዎች ከአግባቢ ሥምምነት ለመድረስ፤ ታዛቢዎች እንደሚሉት፤ ከእስካሁኑ ጉድለት ለመማር መፍቀድ፤የአዋቂዎችን ምክር መስማት፤ ከልምድ የተማሩ ወገኖችን አስተምሕሮ መጠቀም ይገባቸዋል።
                         
መጠቀም ይቻላል።ይፈለጋል ወይ እንጂ ጥያቄዉ።አቶ ግርማ ለጥያቄዉ ጥያቄ ነዉ መስላቸዉ።ምክርም የሚሰማ አለወይ እያሉ።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

 


  


 

Audios and videos on the topic