የኢህአዴግ ም/ቤት መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 29.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኢህአዴግ ም/ቤት መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር «ኢህአዴግ» ምክር ቤት ባለፈዉ ሳምንት ባካሄዴዉ ስብሰባ «ከአገራዊው እድገቱ ጋር ተያይዘው የተቀሰቀሱ አዳዲስ የሕዝብ ፍላጎቶች» እንደተከሰቱና ከፓርቲዉ «አመራር ጀምሮ በሚፈፀሙ ድክመቶች የተነሳ የሕዝብ ቅሬታ» መበራከቱን ባወጣዉ መግለጫዉ ጠቅሰዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:20

ኢህአዴግ

ይህ ከአገሪቱ እድገት ጋር ተያይዞ ተነሱ የተባሉትን ቅራኔዎች የመንግስት ኮሙኒኬሼን የሕዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አቶ መሃመድ ሳይድ እንድያብራሩልን ጠይቀን ነበር።

ይህን የምክር ቤቱ መግለጫ እንዴት ትመለከቱታላችሁ ብለን የአድማጮቻችን አስታያየትም ጠይቅናል። በደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪ ነኝ ያሉና ስማቸዉ ለደኅነት ምክንያት እንዳይጠቀስ የጠየቁ፤ የወጣዉ መግለጫ «ሕዝብን ለመሸወድ»ና «ተቃዉሞዉን ለመቀልበስ» የወጣ ይመስለኛል ሲሉ ተናግረዋል።

በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተቀሰቀሱት ተቃዉሞች ለዜጎችና ለፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት ቢሆንም ኢትዮጵያ «ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ጥንካሬና ምቹ ሁኔታ ላይ ትገኛለች» ሲል መግለጫዉ ያትታል።

በወልቃይ ጠገዴ ጉዳይን አስመልክቶ ምክር ቤቱ ያወጣዉ መግለጫ ፍትኃዊ አይደልም ሲሉ የመቀሌ ነዋሪ የሆኑትና ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በሳምንቱ መጨረሻ በጎጃምና አካባቢዉ በርካታ የተቃዉሞ ሰልፎች እንደታዩም ተዘግቦአል። «ኢህአዴግ» ምክር ቤት በተመለከተ የፌስ-ቡክ ድረ ገጻችን ተከታታዮች ባስቀመጡልን አስተያየት መሰረት አብዣኞቹ ስለ ወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ለትግራይ ክልል መተዉ አልነበረበትም ሲሉ ሌሎች ደግሞ ይህ መግለጫ ምንም የሚፈይደዉ ነገር የለም ሲሉ አስተያየታቸዉን አጋርተዉናል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic