የአፍጋህኒስታን ምርጫን ኦባማና የተመድ አወደሱ | ዓለም | DW | 06.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የአፍጋህኒስታን ምርጫን ኦባማና የተመድ አወደሱ

በትናንቱ የአፍጋኒስታን ምርጫ ምንም እንኳን እስልምና አክራሪው የታሊባን ታጣቂ ቡድን ጥቃት እንደሚዘነዝር ዝቶ የነበረ ቢሆንም፤ ለምርጫው በርካታ ሕዝብ መውጣቱን እንደሚያደንቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ገለፀ።

በትናንቱን ምርጫግድያ የታከለበት በርካታ ግጭት ቢከሰትም፤ ምርጫው ስኬታማ ነበር ሲል የተመድ አድንቋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በበኩላቸው ትናንት አፍጋኒስታን ውስጥ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሀገሪቷ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የተደረገ አንድ ወሳኝ ርምጃ ነበር ሲሉ አወድሰዋል። መራጮቹ በዚህ ታሪካዊ ምርጫ ከፍተኛ ፍላጎት በማሳየት መሳተፋቸውንም ኦባማ ተናግረዋል። ምንም እንኳን በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሰዉ እስልምና አክራሪዉ የታሊባን ሽምቅ ተዋጊ ቡድን በተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚጥል በማስፈራራት ምርጫውን ለማደናቀፍ ሙከራ ቢያደርግም ለምርጫ ከተጠራው 12 ሚሊዮን ህዝብ ሰባት ሚሊዮን የሚሆነው በምርጫው መሳተፉን የምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል። ለምርጫ የቀረቡት 2 እጩዎች ከወዲሁ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ምርጫውን አጣጥለዋል።

በሌላ ዜና አፍጋኒስታን ውስጥ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከተካሄደ ከአንድ ቀን በኋላ ኩንዱስ ውስጥ በተጣለ ጥቃት ሁለት የምርጫ ኮሚሽኑ ሰራተኞች እና አንድ ፖሊስ መገደላቸው ተገልጿል። ሟቾቹ ወደ ኩንዱስ ከተማ ይዘውት በመጓዝ ላይ የነበረው ድምፅ የተሰጠበት ሳጥን በደረሰው ጥቃት መውደሙን አንድ የፖሊስ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። በአጠቃላይ ግን ምርጫው ከተሰጋው በተሻለ መልኩ መካሄዱ ተዘግቧል።

በአፍጋህኒስታን ምርጫ የፀጥታ አስከባሪ ወታደር

በአፍጋህኒስታን ምርጫ የፀጥታ አስከባሪ ወታደር

ትናንት የሚካሄደዉን ምርጫ ለመዘገብ በዝግጅት ላይ ሳለች ከትናንት በስትያ አንዲት ዓለማቀፍ እዉቅናን ያገኘች ጀርመናዊት የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ መገደልዋ ይታወቃል። እንደ አሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ ጀርመናዊቷ ዋየፎቶግራፍ ጋዜጠኛ አንያኒድሪንግ ሃዉስ ከትናንት በስትያ አርብ የተገደለችዉ ከአንድ የአፍጋኒስታን ፖሊስ በተከፈተባት ተኩስ በጥይት ተደብድባ ነዉ። አብራት የነበረችዉ ካናዳዊት ጋዜጠኛ በፅኑዕ ቆስላ እዝያዉ አፍጋኒስታን የህክምና ክትትል ላይ መሆንዋ ተመልክቶአል። በሌላ በኩል በአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተደረገ ባለበት በትናንትናው ዕለት፤ የጀርመንዋ የመከላከያ ሚንስትር ኡዙላ ፎንደር ላየን የጀርመን ጦር በአፍጋኒስታን ስላደረገዉ የተሳካ ተዕልኮ አወድሰዋል። ሚንስትሯ ትናንት «ቢልድ» ለተሰኘዉ ጋዜጣ በሰጡት ቃል ምንም እንኳ የጀርመን ጦርበ አፍጋኒስታን አመርቂ ተግባር ቢፈፅምም፤ በተልዕኮ የወደቁ የጦሩን አባላት ጀርመን የሚረሳዉ አይሆንም። እንድያም ሆኖ የጀርመን ተልዕኮ ለሀገሪቱ ነዋሪ ብዙ መሻሻልን አምጥቷል ሲሉ ፎንድር ላይን ተናግረዋል። በአፍጋኒስታን ከትናንት በስትያ ወደ ስምንት ሚሊዮን ህጻናት ትምህርት ቤት መሄድ ችለዋል፤ ከስምንት ሚሊዮን ህጻናት መካከል ደግሞ ገሚሱ ሴቶች መሆናቸዉ ተመልክቷል። በአፍጋኒስታን በአሁኑ ወቅት ያለዉ አዲስ ትዉልድ አብዛኛዉ መጻፍ እና ማንበብ እንደሚችልም ተዘግቧል። ምንም እንኳን በአሁኑ ግዜ በሀገሪቱ በየቦታዉ ጥቃት እየታየ ህዝቡ ለምርጫ ቢወጣም፤ እንዲህ አይነቱ ርምጃ በታሊባን አስተዳደር አለመታየቱን የጀርመንዋ የመከላከያሚ ንስትር ኡዙላ ፎንደር ላየን ተናግረዋል። የጀርመን የልማት ትብብር ሚንስትር ጌርድ ሙለር በበኩላቸዉ አዲስ የሚመረጠዉ የአፍጋኒስታን መንግስት፤ ለዉጭ ሀገር መዋዕለንዋይ አፍሳሾች፤ የተሻለ አሰራርን ይዞ እንዲቀርብ ከወዲሁ ጠይቀዋል።

አጠቃላይ የምርጫው ውጤት እስኪገለጽ ድረስ ቢያንስ አንድ ሣምምንት ሊፈጅ እንደሚችል ተጠቅሷል። ከተፎካካሪዎች መካከል ለፕሬዚዳንትነት የተቀመጠውን መቀመቻ ከግማሽ በላይ የሚያሸንፍ ካልተገኘ ድጋሚ ምርጫ ግንቦት ወር ውስጥ ሊካሄድ እንደሚችልም ተገልጿል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ